Page 100 - አብን
P. 100
አብን
ከንግድ ስራ የሚገኝ ገቢን በተለመከተ
የስራ ፈጠራን ለማበረታት እና ለወጣቶች የስራ ዕድል
ለመፍጠር ያስችል ዘንድ በጥናት የሚለዩ አነስተኛ ነጋዴዎች
ለአንድ ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ ይሆናሉ፡፡
ህብረትስራማህበራትከማናቸውም የገቢ ግብር ነፃ
ይሆናሉ፡፡
በዘመኑ አዲስ የተፈጠረውን ማህበራዊ ኃላፊነት
ከንግድ ጋር አጣምሮ የሚሰራ የንግድ ስራ ወይም
(social enterpize) የገቢ ግብር ምጣኔ 10%
ይሆናል፡፡ በዘመን አፈራሽ የማህራዊ መገናኛ ዘዴዎች
ለምሳሌ ዩቲዩብና የመሳሰሉት ከሚገኝ የተጠራ ገቢ
20% ግብር ምጣኔ ይመለከታል፡፡
2. የበጀት ፓሊሲ
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሃገሮች መንግስት ውጭውን
በሚሰበስበው ልክ ብቻ እንዲያደርግ ማስቻል ባይቻልም የበጀት
ጉድለቱ ግን በመሰረታዊነት የመጣው አግባብነት በሌለው ልቅ
የሆነ የመንግሰት ወጭ መሆን የለበትም፡፡ የበጀት ጉደለቱን
ለመሙላት የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛውን ግዜ የሚገኘው
በብድር የሚመጣ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነን የዕዳ
ጫና በሃገሪቱ ላይ ያስከትላል፡፡ ይህን ለመቀነስም ሲባል
መንግስትበጀቱን ፈሰስ የሚያደርግባቸው ዘርፎችና ፕሮጀክቶች
በምላሹ የሚገኝ ገቢብደርን ለመመለስ ከሚወጣው ወጭ
የተሻለ ገቢ /ጥቅም እንደሚያስገኝ በጥናት የተረጋገጠና
98 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !