Page 105 - አብን
P. 105
አብን
ይደረግላቸዋል፡፡ አበርክቷቸው በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በግብር
ምንጭነት፣ በውጭ ምንዛሬ ዕድገት፣ በምርቶች አቅርቦትና
ዋጋ ተወዳዳሪነት፣ በቴክኖሎጅ ሽግግርና በሌሎችም ዘርፎች
ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን የመንግስት ቢሮክራሲ የማዘመን
ሥራ ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን ንቅናቄያችን ይገነዘባል፡፡
እስካሁን ከሁሉም የልማት መሠረቶች በላይ ችግር ሆኖ
የቆየው የኃይል አቅርቦት ችግር ነው፡፡ አብን መንግሥት
በሚሆንበት ጊዜ ዋናውን መንግስታዊ አቅሙን እዚህ ላይ
አሟጦ በመጠቀም ይሄንን ችግር ይቀርፋል፡፡ ኢንቨስትመንቶች
መዋቅራዊ ሽግግር በሚያመጡ ዘርፎች ላይ ማድረግ አስፈላጊ
ነው፡፡ ከፈቃድ አወጣጥ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከማጓጓዣ
ዘዴዎች እጥረት፣ ከግብዓት እጥረትና የመሳሰሉትን ችግሮች
መፍታት ያስፈልጋል፡፡ አብን ከኢንቨስትመንት አንፃር ዋና
ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ፣
በንብረት ጥበቃና በኢንቨስትመንት ዋስትና ላይ ይሆናል፡፡
2. የገበያ ሥርዓት
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በምጣኔ ኃብት ዘርፍ ተጠቃሚ
ሊሆን የሚችለውና ዋናዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎች ዕውን
የሚሆኑት ሀገራዊው የምርትና የገበያ ሥርዓት ውቅር
ወቅቱንና መጭውን ዘመን መዋጀት ሲችል ነው፡፡
አብን በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ እንዳሰፈረው ለዘብተኛ
ሊበራሊዝም የፖለቲካል ኢኮኖሚ ፍልስፍና ይከተላል፡፡
ይኸውም ራዕያችን የኢትዮጵያ የወደፊት የኢኮኖሚ እድገት
እና አጠቃላይ የልማት ስኬት ቀጣይነት ባለው፣ የተነቃቃ፣
የማናቸውንም መሰናክል መቋቋም የሚችል፣ ሊኖር በማይችል
103 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !