Page 103 - አብን
P. 103

አብን


             እንደተገለጸው         ምክንያታዊ        የግብር      ምጣኔ       ማስቀመጥ

             እንዲሁም  ህገ-ወጥ  ንግድን  መቆጣጠር  ከፍተኛ  ትኩረት
             የምንሰጠው ጉዳይ ይሆናል፡፡የሀገር ውስጥ ንግድ መስፋፋትና
             መቀላጠፍ ለማስቻል በምርቶች ዘርፍ ስፔሻላይዜሽን እንዲኖር
             ያደርጋል፡፡  የሀገር  ውስጥ  ንግድ  እንዲበረታታ  ከሀገር  ውስጥ
             እቃዎች  ዝውውር  ጋር  ያለውን  የቀረጥ  አሠራር  ማስተካከል
             ይገባል፡፡  ይኸውም  በሁሉም  የፌዴራሉ  ግዛቶች  ውስጥ  ወጥ
             የሆነ  አሠራር  እንዲዘረጋና  ግዛቶችን  የሚያስተሳስር  አሠራር
             እንዲኖር  እናደርጋለን፡፡  በተጨማሪም  የባቡር፣  የመንገድና

             የአየር  ትራንስፖርት  እንዲስፋፋና  እንዲዘምን  ይሠራል፡፡
             ተንቀሳቅሶ  የመሥራትና  በየትኛውም  የሀገሪቱ  ድንበር  ውስጥ
             ኃብት የማፍራት መብትን በጽናት እናስፈጽማለን፡፡ዓለም አቀፍ
             ንግድን ከማበረታታት አንፃር የኢኮኖሚ ዕድገቱን በማስፈንጠር
             ረገድ  ትልቅ  ሚና  ያላቸውን  ምርቶች  ለሚያስመጡ  አካላት
             የቀረጥ  ቅነሳ  ይደረጋል፡፡  ይኸም  በባለሙያዎች  በሚመራ

             አሠራር  ተፈጻሚ  እንዲሆን  ይደረጋል፡፡  የውጭ  ምንዛሬ
             አስተዳደር በመንግስት የመሆኑ ጉዳይ በጊዜ ሂደት እንዲሻሻል
             የሚያደርግ  ሥራ  ይሠራል፡፡  ያንን  ለማድረግ  አስቻይ
             ሁኔታዎች  እስኪፈጠሩ  ድረስ  የመንግስት  የውጭ  ምንዛሬ
             አቅርቦት  ቀድመው  በተለዩ  አሠራሮችና  መስፈርቶች  በግልጽ
             በተቀመጠ  መንገድ  እንዲከወን  እናደርጋለን፡፡  ይህ  ዘርፍ
             ከብሔራዊ  አድሎ፣  ከሙስና  እና  ከአሻጥር  ተላቆ  ለሀገር
             ጥቅም በሚያመች መንገድ እንዲፈጸም ይደረጋል፡፡


             በአንጻራዊነት  በዝቅተኛ  ወጭ  በሀገር  ውስጥ  መመረት
             የሚችሉ  ምርቶችን  ከውጭ  ማስገባት  የውጭ  ምንዛሬ

             ስለሚሻሙ  በሀገር  ውስጥ  እንዲመረቱ  የተለያዩ  የማትጊያ
             101    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   98   99   100   101   102   103   104   105   106   107   108