Page 98 - አብን
P. 98
አብን
ተጨማሪ እሴት ታክስ ማለት ከመሰረታዊ ፍጆታ ላቅ ያለና
እሴት የጨመረ ግብይት ላይ የሚጣል ግብር ነው፡፡ ነገር
ግን በአገራችን አሁን ላይ እየተተገበረ ያለው የታክስ ስርዓት
መሰረታዊ የኑሮ ፍላጎቶችን እና የቅንጦት እቃዎች እና
አገልግሎቶችን ያልለየ እኩል ታክስ የሚጣልበት ነው ፡፡
በመሆኑም፡-
መሰረታዊ የምግብ ነክ ሸቀጣቀጦች በሙሉ ከዚህ
ግብር ነፃ እናደርጋለን፡፡
የግብር ምጣኔውን እንደ እቃዎቹና አገልግሎቶች
አይነት በጥናት ላይ ተመስርተን ማስተካከያ
እናደርጋለን፡፡ ለማህረሰቡ በጣም አስፈለጊ የሆኑት
ዕቃና አገልግሎቶችን የታክስ ምጣኔ በልዩ ሁኔታ
ማስተካከያ እናደርጋለን፡፡
በዘርፉ ተብሎ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ
አንዲሆን የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን አናስቀራለን፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ዝቅተኛ በግዴታ
መመዝገቢያ መሰፈርት ዓመታዊ ሽያጭ መጠን
ከብር 2,000,000 በላይ እንዲሆን እና ሌሎች
በፈቃደኛነት የሚመዘገቡበት አሰራር ይዘረጋል፡፡
ኤክስያዝ ታክስ
ዘመናዊነትን በሚያስድግ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀምና
ማላመድ እንዲያስችል ከዚህ ቀደም ቅንጦት ተብለው
የተመደቡ ዕቃዎች ላይ የተጣሉ ኤክሳይስ ታክስ ላይ
ማሻሻያእናደርጋለን፡
96 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !