Page 99 - አብን
P. 99

አብን


                          የተርን ኦቨር ታክስ

             የተርን  ኦቨር  ታክስ  ምጣኔን  በዕቃ  እና  ለአገልግሎት  ዘርፍ
             ማስተካከያ እናደርጋለን፡

                          ቀጥተኛ ግብርን በተመለከተ
             በአገራችን  የታክስ  አስተዳደሩ  ደካማ  በመሆኑ  72%  ገቢውን
             የሚሸፈነው  በቀላሉ  ከሚገኘው  በመቅጠር  የሚሰበሰብ  ግብር
             ነው፡፡  እንዲሁም  ንግድ  ማህበራት  30%  የትርፍ  ግብር
             እየከፈሉ  በዝቅተኛ  ኑሮ  የሚኖረው  ተቀጣሪውና  የግል

             ነጋዴዎች  35%  እንዲከፍሉ  ይደረጋል፡፡  የግብር  ምጣኔ
             ከፍተኛ  ማድረግ  ለግብር  ስወራ  ያጋልጣል፡፡  ስለሆነም  ይህን
             የሚፈታ  የፖሊሲ  አቅጣጫ  ተግባራዊ  ይደረጋል፡፡  ይህን
             መሰረት  አድርገን  ከገቢ  ጋር  እያደገ  የሚሄድ  (progresive)
             የሆነውን       የታክስ       ስርዓት      ቀይረን       ወደ     ተመጣጠነ
             (proportional)  ስርዓት እንቀይራለን፡፡


                          ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ
             ገቢው 1500 ብር በታች የሆኑ ሁሉ ከግበር ነፃ እናደርጋለን፡፡
             ከመቀጠር  የሚገኝ  ገቢ  የግብር  ምጣኔ  ተመጣጣኝ  ስርዓት
             ተግባራዊ በማድረግ በጥናት መሰረት ይወሰናል፡፡ ይህም ሰዎች
             ተጨማሪ  ስራ  እንዲሰሩ  እና  ምርታማነትን  የሚያበረታታ
             ይሆናል፡፡











               97   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   94   95   96   97   98   99   100   101   102   103   104