Page 106 - አብን
P. 106
አብን
የነፃ ገበያ መርሆ ሳይሆን ግልፅነት ባለው ከፖለቲካ
ጣልቃገብነት የፀዳ፣ በውድድር ላይ በተመሰረተ የገበያ
ኢኮኖሚ መርሆዎች የሚመራ የኢኮኖሚ እድገት እውን
የሚያደርግ ስርዓት መገንባት ነው፡፡ይኸውም የገበያ ክፈተት
ሲፈጠር መንግስት ክፍተቱን እየሞላና የግሉን ዘርፍ
እያበረታታ የሚሄድበት ሥርዓት ነው፡፡
ንቅናቄያችን አብን በአንድ በኩል መንግስት ወጭ ቆጣቢ
ባልሆኑና የግሉ ዘርፍ ሊሠራቸው በሚችሉ እንዲሁም ዜጎች
ያለችግር ግብይት የሚፈጽሙባቸውን ዘርፎች ለቆ መውጣት
ይገባዋል ብሎ ያምናል፡፡ ይህ የመንግስት ወጭ ቆጣቢነትም
ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለውጭ ንግድ ዕድገት፣ለሥራ ፈጠራና
ተያያዥ ጉዳዮች የተሻለ ጥቅም ያላቸው ዘርፎች የታክስ ቅነሳ
እንዲደረግላቸው ያስችላል፡፡
የኢኮኖሚ ሥርዓታችን በግሉ ዘርፍ ካፒታል በከፍተኛ ፍጥነት
እንዲዳብር ምቹ ሁኔታን መፍጠር ላይ ትልቁን ትኩረት
ማድረግ አለበት የሚል ፅኑ እምነት አለው፡፡
ይህ የሚሆነው ደግሞ ስትራቴጂክ ጥቅም በሌላቸውና የግሉ
ዘርፍ ሊዘውራቸው ከሚችላቸው ዘርፎች መውጣትና ርባናው
ዝቅተኛ የሆነ የመንግስት ወጭን መቀነስ ሲቻል ነው፡፡
በተጨማሪም ቢዝነስ መስራትን ቀላል በሚያደርግ መንገድ
የመንግስት አገልግሎትን ማቀላጠፍ ይገባል፡፡ መንግስት
በዋናነት መሠረተ ልማትን በማስፋፋትና የገበያ ጉድለቶችን
በማቃናት ላይ ራሱን ሊጠምድ ይገባል፡፡
የመንግስት በጀት አስተዳደርም ለህዝብ ግልጽነት ያለው ሆኖ
መፈጸም ይገባዋል፡፡
104 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !