Page 111 - አብን
P. 111
አብን
አካታች እና ተደራሽ የሆነ የፋይናንስ ሥርዓት
እንዲኖር እና ተጠቃሚውን የመከላከል (consumer
protection)፤
የፋይናንስ ሥርዓቱ የተረጋጋ እና ዋስትና ያለው
እንዲሆን ማድረግ፤
የመረጃ ሥርጭት ለማሳደግ፤
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ዓለማዎች ለማሳከት
የሚከተሉት ለውጦችን ተግባራዊ ያካሄዳል፡፡
የፋይናስ ሥርዓቱን አወቃቀር በተመለከተ
የፋይናንስ ሥርዓቱ በብሔራዊ ባንክ ተቆጣጣሪነት በዋነኝነት
በንግድ ባንኮች፣ የልማት ባንክ፣የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና
አነስተኛ ወይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የተዋቀረ ነው፡፡
የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ የካፒታል ገበያ እና ጠንካራ የገንዘብ
ገበያ (money market) በዘርፉ ባለመኖራቸው የፋይናንስ
ሥርዓቱ ጠንካራ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ በመሆኑም
ድርጅታችን፦
የካፒታል እና የገንዘብ ገበያ (capital and money
market) ልማት፦ ድርጅታችን የረዥም ጊዜ እና
የአጭር ጊዜ ብድር አቅርቦትን ለማሳዳግ፤ ለተበዳሪው
የብድር ወለድን እርካሽ እና ተመጣጣኝ ለማድረግ
እንዲሁም ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ይረዳ ዘንድ
ጠንካራ የካፒታል ገበያ እንዲቋቋም እና የተደራጀ
የገንዘብ ገበያ እንዲኖር የሚረዱ የፖሊሲ እና የሕግ
ማዕቀፎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
109 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !