Page 115 - አብን
P. 115
አብን
ማኅበረሰብ ዘንድ ሊሰሩ በማይችሉ ነገር ግን ምርትና
ምርታማነትን ሊያሳድጉ በሚችሉ መስኮች ላይ ትኩረት
አድርጎ ይሰራል፡፡ ከነዚህም መካከል፦
በአገር ውስጥ መመረት እየቻሉ ከወጭ በሚገቡ እጥረት
በሚታይባቸው የፍጆታ እቃዎች ላይ በአገር ውስጥ
ማምረት የሚያስችሉ ፕሮጅክቶቸ (ዘይት፣ ስኳር ወዘተ.)
መደገፍ፤
መሰረተ ልማት ግንባታ እና ተደራሽነት (መንገድ፣ ውሃ፣
መብራት፣ )
ጤና እና ትምህርት
የኃይል መመንጫና ማሰረጫ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ
መቀጠል፤
የግብርናውን ዘርፍ የሚያዘምኑ ምርምርና ፕሮጀክቶች
መደገፍ፤
ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚያስችሉ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅና ዲጂታል ኢኮኖሚን መደገፍ፤
የከባቢ አየር ብክለትን ቁጥጥር በማድረግ አረንጓዴና
ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር አስቻይ
ሁኔታዎችን መፍጠር የሚሉ ናቸው፡፡
2.3 ግብርና ገጠር ልማት
የአብን ግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ የሚከተሉት የፖሊሲ
አቅጣጫዎች (policy directives) ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
113 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !