Page 118 - አብን
P. 118
አብን
ኪራይ እየሰበሰቡ ያሉትን መሬቱን በመንጠቅ ሊያለማ
ለሚችል ማስተላለፍ ይገባል፡፡ወደ ስራ የገቡት ባላሀብቶች
የእርሻ ማሽኖችንና ለኢንቨስትመንቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች
ከታክስ ነጻ የሚገቡበትን ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
ከግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የግል ተቋማት ከገበያው
እንዲወጡ እና የመንግስት / ጥገኛ ኢንተርፕራይዞች
በብቸኝነት እንዲቆጣጠሩት በመደረጉ የግብዓት አጠቃቀም
ደካማነት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም አርሶ አደሩ
በመንግስት ሁለንተናዊ ቁጥጥር ውስጥ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በመሆኑም የግብዓት አቅርቦት አገልግሎት ለግሉ ዘርፍ ክፍት
መደረግ አለበት ብሎ አብን ያምናል፡፡
2.3.2 እንስሳት እርባታ
የእንስሳት ምርት እና ምርታማነትን ለማሻሻል የእንስሳት
ጤና፣ የወተት እርባታ፣ የዶሮ እርባታ፣ ቆዳና ሌጦ፣ የቁም
እንስሳትና ሥጋ፣ እርባታ፣ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ
አደር ልማት፣ እና የዝርያ ማሻሻል፣ ግብርና ምርምር እና
የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት
እንደሚያስፈልግ አብን በፅኑ ያምናል፡፡
የእንስሳት ጤና ማሻሻል
የእንስሳት፣ ጤና ስትራቴጂ በማዘጋጀት ሁሉንም የእንስሳት
ጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ አሁን ያለውን (30%
ብቻ) የእንስሳት ህክምና ተደራሽነት ከፍ በማድረግ የእንስሳትን
116 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !