Page 122 - አብን
P. 122

አብን


             መንጋ  እና  ባሕላዊ  አሰራር  ወደ  ዘመናዊ  በማሻሻል

             እየተመናመነ የመጣውን የንብ ቀሰም እጽዋት በማልማት እና
             የምርት  ጥራትን  የሚያሻሽሉ  ቴክኖሎጅ  በመጠቀም  ጥራቱን
             የጠበቀ  ኦርጋኒክ  ማር  ለገበያ  ማቅረብ  ትኩረት  የሚሰጠው
             ነው፡፡

                      የመሬት አቅርቦት
             የእንስሳት  እርባታ  ከዘርፉ  ባህሪ  ወሳኝ  እና  ለምርት  ማነቆ
             ከሆኑት  አንዱ  መሬት  ነው፡፡  የመሬት  እጥረት  በእንስሳት

             እርባታ  ውስጥ  በጣም  ወሳኝ  ችግር  ለሆነው  የእንስሳት  መኖ
             እጥረት  ምክንያት  ነው፡፡አሁን  ያለውን  ቢሮክራሲ  በማሳጠር
             በፍጥነት  ወደ  ተግባር  ለሚገባ  አርሶ  አደር  መሬት  የማቅረብ
             ሥራ  አንዱ  ሲሆን  የመሬት  እጥረት  ባለባቸው  አካባቢዎች
             ምርቱን  በኮንትራት  አርሶ  አደሩ  የሚያመርትበትን  እና
             ባለሀብቶች  የማቀነባበር  እና  ለገበያ  በማቅረብ  ተሳስረው

             የሚሰሩበት  ሥርዓት  ይመቻቻል፡፡  በሌላ  በኩል  ከመሬት
             ፖሊሲው  መሻሻል  ጋር  ተያይዞ  መሬት  ከግለሰቦች  በመግዛት
             እና በመከራየት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡

                      ምርምር
             የምርምር ተቋማትን በማጠናከር የእንስሳት  ዝርያን  በማሻሻል
             እና  አዳዲስ  ሳይንሳዊ  አሰራሮችን  በማውጣት  የእንስሳት
             ምርታማነት  እንዲያድግ  ይደረጋል፡፡ይህም  አዳዲስ  ዝርያ

             ማላመድን  እና  በምርምር  በማውጣት  ለአርሶ  አደሩ
             ማሰራጨት ቁልፉ ሥራ ይሆናል፡፡



             120    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   117   118   119   120   121   122   123   124   125   126   127