Page 121 - አብን
P. 121
አብን
ድርሻ ይይዛል፡፡ ከዚህም የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ
ለማሳደግና በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በሕገ- ወጥ በድንበር
አካባቢ የሚገበያየውን እና ወደ ውጭ የሚላከውን ከፍተኛ
ቁጥር ያለው የቀንድ ከብት ላይ የቁጥጥር ሥርዓት
በመዘርጋት እንዲቆም ይደረጋል፡፡ በቁም እንስሳት እና ቀይ
ሥጋ ግብይት በሕጋዊ መንገድ የተሰማሩትን አካላት ብድር
በማቅረብ፣ የብድር ደብዳቤዎችን ማመቻቸት (ሌተር ኦፍ
ክሬዲት)፣ ማስተዋወቅ እና ላኪዎች ከአስመጪዎች ጋር
የውል አፈፃፀም የመደገፍ ሥራዎች እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
ጥራት በማረጋገጥ፤ የግብይት ወጪዎችን መቆጣጠር እና
ዝቅ በማድረግ ግብይቱን ውጤታማ የሚያደርግ አሰራር
ይዘረጋል፡፡ የኢትዮጵያ ስጋ ጣዕም እና ኦርጋኒክ በመሆኑ
በአረብ አገራት ተመራጭ ከመሆኑ አንጻር የንግድ ምልክት
አግኝቶ ተወዳዳሪ በመሆን ለገበያ እንዲቀርብ ሰፊ ሥራ
ይሰራል፡፡
ንብ እርባታ
በንብ ኃብት በአፍሪካ የተሻለ ደረጃ ላይ የምትገኛው አገራችን
ኃብቱን በሚገባ አልተጠቀመችበትም፡፡ይህ ዘርፍ የሰም እና
ማር ምርት በማምረት ለአውሮፓ እና ለሌሎችም ገበያ
በማቅረብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ቢሆንም በሰፊው ትኩረት
ተሰጥቶ አልተሰራበትም፡፡በተለይ በጣዕም እና ኦርጋኒክነቱ
የታወቀው የማር ምርታችን በአውሮፓ ገበያ በጣም ተፈላጊነት
አለው፡፡ በአሁኑ ወቅት የሚመረተው ምርት በጥራት
ምክንያት በአገር ውስጥ ገበያ እንኳ ተፈላጊ ባለመሆኑ
አምራቹ በዝቅተኛ ዋጋ ይሸጣል፡፡አሁን ያለውን ሰፊ የንብ
119 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !