Page 125 - አብን
P. 125

አብን


             2.4.   ኢንዱስትሪ፣ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን
                2.4.1  ኢንዱስተሪ ልማት
             የአገራችን  የኢንዱስትሪ  ዘርፍ  ገና  በጀምር  ሂደት  ላይ  ያለ
             ነው፡፡በመሆኑም  ግብርናውን  የሚያግዝና  ተመጋጋቢ  የሆነ፤
             ለወጣቶች  የሥራ  እድል  የሚፈጥሩ፤ከተሜነትን  የሚያመጡ
             የኢንዱስትሪ  አማራጮች  እየተገመገሙ  በጥናት  ይገነባሉ፡፡
             የአብዛኛው ሕዝብ አኗኗር በግብርና ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ
             አንፃር  ግብርናውን  የሚያዘምኑ  እና  ለግብርናው  ግብዓት
             የሚሆኑ         ብሎም        ከግብርናው          ግብዓት        የሚቀበሉ

             ኢንዱስትሪዎች  ላይ  በዋናነት  ትኩረት  ተደርጎ  ይሰራል፡፡
             ኢንዱስትሪው  የገቢ  ምርቶችንና  ጥሬ  ዕቃዎችን  የሚተካ
             እንዲሆን  ይበረታታል፡፡  ገበሬዎችን  በዩንዬንና  በኅብረት  ሥራ
             ማኅበራት        በማደራጀት        የግብርና       ምርቶች       ማቀነባበሪያ
             ኢንዱስትሪዎችን           እንዲያቋቁሙ          መንግስት        ልዩ     እገዛ
             ያደርጋል፡፡ ለአጠቃላይ አገራዊ  ዕድገት  አዋጭ የሆኑ  ዘርፎች

             ተለይተው  በዘርፉ  ለሚሰማሩ  ባለሀብቶች  የግብር  እፎይታ
             ጊዜን ጨምሮ ከቀረጥ ነፃ የሆነ አሰራር ይተገበራል፡፡ በውጭ
             አገር  የሚኖሩ  ትውልደ  ኢትዮጵያን  በኢንዱስትሪ  ግንባታው
             እንዲሳተፉ ለማበረታታት ሲባል ልዩ እገዛ ይደረጋል፡፡ በውጭ
             አገር  ያለውን  ኃብት፤ጉልበትና  እውቀት  በአገር  ውስጥ
             ኢንቨስትመንት ለመጠቀም ሲባል ከመያዣና ከግብር ነፃ የሆነ
             አሰራር ይዘረጋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠርና ብዙ
             ሰው  ኃይል  ሊያሳትፉ  የሚችሉ  ትንንሽ  ኢንዱስትሪዎችን

             ለማበረታት  የገንዘብ  ብድርን  ጨምሮ  የመስሪያ  ቦታና የግብር
             እፎይታ  ጊዜ  እንዲሰጥ  ይደረጋል፡፡ኢኮኖሚው  አሁን  ካለው
             ግብርና  መር  ወደ  ኢንዱስትሪ  መር  እንዲሸጋገር  ታስቦ


             123    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   120   121   122   123   124   125   126   127   128   129   130