Page 128 - አብን
P. 128

አብን




             ሐ.)የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፦
             በከተሞች ላይ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ መሰረታዊ ችግር ነው ፡፡
             ለአብነት  76%  በላይ  የሚሆነው  የአዲስ  አበባ  ሕዝብ  በቀበሌ
             /በመንግስት  ቤት/  እና  በግለሰብ  ቤት  ውስጥ  ተከራይቶ
             የሚኖርና  የራሱ  መጠለያ  የሌለው  ነው፡፡  የመኖሪያ  ቤት
             ችግርን  ለመፍታት  ቤት  ሰሪዎች  ራሳቸውን  በማህበር
             እንዲደራጁ  በማድረግ፣  የባንክ  ብድር  በማመቻቸት፣  የግንባታ
             ግብዓት  ከቀረጥ  ነፃ  በመፍቀድ፣የግንባታ  ቁጥጥር  እገዛ

             በመስጠት በራሳቸው እንዲያስገነቡ በማድረግ እንዲሁም የአገር
             ውስጥና  የውጭ  ባለኃብቶች  በዘርፉ  እንዲሰማሩ  ይደረጋል፡፡
             መንግስት  ‘የቤት  ሥራ  ኘሮጀክት’  በሚል  የራሱን  የሪል
             እስቴት የንግድ ድርጅት በማቋቋም የቤት ፈላጊዎችን ፍላጎት
             ለማሟላት  የሄደበት  ርቀት  ከ15  ዓመት  በላይ  ጊዜ  ወስዶም
             ቢሆን  ከቤት  ፈላጊው  ብዛት  አኳያ  እጅግ  በጣም  ትንሽ

             የሚሆነው በዕጣ የተጠናቀቁና ያልተጠናቀቁ ቤቶችን ለማግኘት
             ቢያስችልም  ለአብዛኛው  ሕዝብ  የመኖሪያ  ቤት  እድሜ  ልክ
             የማይሳካ  ፍላጎት  ሆኗል፡፡  በመሆኑም  በመንግስት  እጅ  ያሉ
             ፕሮጀክቶችን  ከፍተኛ  ልምድ  ካላቸው  የሀገር  ውስጥ  እና
             የውጭ  ቤት  አልሚዎች  ጋር  በጋራ  በሽርክና  የሚሰሩበትን
             አሰራር በመዘርጋት በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ይደረጋል፡፡ በሂደት
             የግል ዘርፉ የቤት ልማት ፕሮጀክትን እንዲረከበው ይደረጋል፡፡


             መ).  የመሬት  ዝግጅትና  የመሬት  ልማት  በሚል  የከተማ
             ነዋሪዎችን ማፈናቀል፡-



             126    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   123   124   125   126   127   128   129   130   131   132   133