Page 132 - አብን
P. 132
አብን
ሸ) ከተማ ማስፋፋት (urbanization) እና የውስጥ ፍልሰት
(internal migration)
የኢትዮጵያ የከተማ መስፋፋት ፍጥነት 4.3 % እንደሆነ
ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ይህ በዚህ ከቀጠለ የመኖሪያ ቤት
እጥረት፤ የውኃ እና ፍሳሽ ችግሮች (water and sanitary)
እንዲሁም የሥራ ማጣት ችግሮች ያስከተትላል፡፡ ከዚህ ባለፈ
በኢትዮጵያ ትልቁ የአገር ውስጥ ፍልሰት ወደ አዲስ አበባ
የሚደረገው ነው፡፡ አዲስ አበባ እና አካባቢዋ 70 በመቶ
የአገሪቷን ኢኮኖሚ (economic congestion) ይዟል፡፡
እንዲሁም የፖለቲካ እና ኮንፈረንስ ማእከል (political
congestion) ማለትም የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና ፓርላማ፣
ቤተመንግስት እንዲሁም የትላልቅ ኢምባሲዎች እና
ቆንስላዎች እና የአፍሪካ እና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ
(resident) አዲስ አበባ ናት። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት አዲስ
አበባ የመኖሪያ ቤት ችግር፣ የትራፊክ (transport) መጨናነቅ
እና የአገልግሎቶች ተደራሽነት እና መቆራርጥ ከፍም ሲል
አለመኖር ሲከሰት ይስተዋላል። ለዚህም እንደ መፍትኼ
ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ ቢወሰድ መልካም የሚሆነው
የፖለቲካ እና ኮንፈረንስ እንዲሁም ኢኮኖሚ ከተሞች
ተለይተው እንደ አማራጭ ዋና ከተሞች ቢወሰዱ ከላይ
የተጠቀሱትን ችግሮች ይቀንሳሉ ኢኮኖሚውም ፍትኃዊ
(spatial economic distribution) ይሆናል ብሎ አብን
ያምናል።
በመሆኑም አብን ለዚህ የሚረዱ ሁለት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን
በሚቀጥለው አስር ዓመት ለመገንባት አቅዷል፡-
130 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !