Page 131 - አብን
P. 131
አብን
- የነባር ከተማ ማሻሻያ ማስተር ኘላን ዝግጅት
በሚመለከት በከተማው ያለውን የእንቅስቃሴ ትስስር
ጥናት ያገናዘበ ዲዛይን በሥራ ላይ እንዲውል
ይደረጋል፡፡
- ከማስተር ኘላን ዲዛይን ዝግጅት ጀምሮ የኅንፃ፣
የመንገድና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ዲዛይን ዝግጅት
በሚመለከት ከፖለቲካ ፍላጎት እና ጣልቃ ገብነት
ውጭ በሆነ መንገድ በባለሙያዎች ምክር ኃሳብ
ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
ኮንስትራክሽን፡-
- በአገራችን ያሉት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት
ብቃት ያለው አደረጃጀትና ደረጃቸውን የጠበቁ
በማድረግ ጥራቱን የጠበቀ ባለሙያ በማፍራት
ለግንባታ ሥራ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት
ትኩረት ይደረጋል፡፡
- የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የግንባታ ዕቃዎች ወደ
አገር ውስጥ የሚገቡና በአገር ውስጥ የሚመረቱ
በመሆኑ የጥራት ደረጃ ለማስጠበቅ የተጠናከረ
ሥርዓትይዘረጋል፡፡
- የአገር ውስጥ ተቋራጮች በአደረጃጀታቸውና በባለሙያ
ክህሎት ማነስ ምክንያት የተቋራጮቹ የደረጀ ጥራት
ደካማ በመሆኑ እና ተወዳዳሪነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየወረደ በመምጣቱ ሀገር በቀል ተቋማትን
የሚያበረታታ እና አቅም የሚገነባ ማዕቀፍ ይዘጋጃል፡፡
129 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !