Page 136 - አብን
P. 136
አብን
ነባር መዳረሻዎችን ብቻ ሳይሆን ከአዳዲስ መዳረሻዎች
ጋር ጭምር በትስስር የማልማት ሥራ ለመስራት
በሚያስችል መልኩ የአጭርና ረዥም ጊዜ እቅድ
ተዘጋጅቶ ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ በየደረጃው ካሉ
ባለድርሻ አካላት ጋር አጥጋቢ ውይይትና ጥናት
እየተደረገባቸው እንዲተገበሩ ይደረጋል፡፡
እየተጠቀመን ያለው ካሉን ኃብቶች እጅግ በጣም
ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ሰፊ የማስተዋወቅ ሥራ
የሚጠየቁትን በመለየት በሁሉም የመገናኛ ብዙኃን
መንገዶች ለአገር ውስጥና ለውጪ አገር ጎብኝዎች
በሚረዱት የቋንቋ አማራጮች ለማቅረብ ይሰራል፡፡
ከአገር ውስጥና ከውጪ የሚዲያ ተቋማትና አስጎብኝ
ድርጅቶችና የጉዞ ወኪሎች፣የኢትዮጵያ አየር
መንገድና ሌሎች የውጪ አገራት አየር መንገዶች ጋር
ሰፊ የሆነ አመርቂ ግንኙነቶችን በመፍጠር ሰፊ የሆነ
የማስተዋወቅ ሥራ እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
የቱሪዝም አገልግሎት ተቋማት የሆኑት
እንደሆቴሎች፣ እንግዳ ማረፊያዎች፣ የመኝታ
አገልግሎት ጥራትና አቅም የማሳደግ፣የቱሪስት መረጃ
ማዕከላት በዋና ዋና መዳረሻ የጉዞ መስመሮች
እንዲደራጁና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ
ተደርገው እንዲሰሩ ጥረት ይደረጋል፡፡
የመዳረሻዎች የጉዞ መስመርና ክዋኔ (tourist routes
and tourism activities) ከመዳረሻዎቹ
መገለጫዎችና ተጨባጭ (destination
characteristics) ሁኔታ አንጻር እንዲዘጋጁ
134 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !