Page 139 - አብን
P. 139
አብን
አገርም እንዲያለማ ሰፊ ድጋፍና ርብርብ ይደረጋል፡፡
ይህም ትልቅ የእውቀትና ልምድ ተሞክሮን በአገር
ውስጥ ለማስፋፋት ሰፊ ሚና እንደሚኖረው
ይታመናል፡፡
የዓለምአቀፍ ተቋማት የኮከብ ደረጃ ምደባ መመዘኛ
እንዳለ ሆኖ ከዛ በታች የሆኑትን ተቋማት አቅምና
ጥራት ለማሳደግ በሕግና መመሪያ የታቀፈ ድጋፍ
ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል፡፡የደረጃ መመዘኛ
መስፈርቶችን በማውጣት ክልላዊና አካባቢያዊ ደረጃ
የማውጣትና ደረጃ የመመደብ ሥራ እንዲሰራ
ይደረጋል፡፡
ሐ. የኅብረተሰብ ተጠቃሚነትና የማኅበረሰብ አቀፍ
ልማት ስርፀትን በተመለከተ
ሕብረተሰቡ የበይ ተመልካች ብቻ ሳይሆን የልማቱ እኩልና
ፍትኃዊ ተቋዳሽ እንዲሆን ለማድረግ፡-
በቱሪስት መዳረሻዎችና የቱሪስት መስህብ
ስፈራዎች አካባቢ ያለው የኅብረተስብ ክፍል ንቁ
ተሳታፊ እንዲሆን የማነቃቃት፣ የማስተማርና
የማሳተፍ ሥራ ይሰራል፡፡
137 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !