Page 138 - አብን
P. 138
አብን
Products) የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራ
ይሰራል፡፡
ለ. የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ልማትን
በተመለከተ
የአገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ኃብት በመጠቀም
የቱሪዝም ልማቱን በማሳደግ ረገድ ለአገር ውስጥና
የአገር ውጭ ቱሪስቶች ጥራት ያለው አገልግሎት
ለመስጠት እንዲያስችል የተገነቡትን በመደገፍና
ተፈላጊውን ሰው ኃይል እንዲያሟሉ ድጋፍ፣
ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል፡፡
እነዚህ ተቋማትም የሕዝቡን ባሕል፣ ኃይማኖት፣
መስህብ ስፈራዎች ከማስተዋዎቅና ከማበረታታት
ባለፈ ከባሕልና እሴት ውጪ የሆኑ ወይም ሊጣረሱ
የሚችሉ አገልግሎቶችና ሊገልፁ የሚችሉ ነገሮችን
በሚከለክል መልኩ መመሪያና የሕግ ማዕቀፍ
ይዘጋጃል፡፡
የእነዚህ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኢንቨስትመንትን
ለማሳደግ በሚደረገው ሁሉ ሂደት የማኅበረሰብ
መዝናኛ ስፍራዎች፣ መናፈሻዎችና ፓርኮች
ዝቅተኛውን የኅበረተሰብ ክፍል እንዲያቀፍ ተደረጎ
በማስተር ፕላን የተዘጋጀ አተገባበር እንዲኖረው
ይደረጋል፡፡
ዲያስፖራው በዘርፉ መዋዕለ ንዋይ እንዲያፈስና
በአገሩ ኃብት እንዲያፈራና ወገኑን እንዲጠቅም
136 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !