Page 133 - አብን
P. 133

አብን




             1.  የጣና ዙሪያ ኢኒሼቲቭ

             በዓለማችን  ላይ  ያሉ  ውድና  ቅንጡ  የመዝናኛ  ከተሞችና
             መኖሪያ  ቦታዎች  የሚገኙት  በኃይቆችና  በወንዞች  ዳርቻዎች
             ነው፡፡  ኢትዮጵያ  ደግሞ  እንደ  ጣና፣  ሃዋሳ፣  ሻላ፣  ላንጋኖ፣
             ጫሞ፣  አባያ፣  የድብረዘይት  ሃቆች፣  አባይ፣  ተከዜ፣  አዋሽ
             ወዘተ  አይነት  ታላቅ  ወንዞችና  ሃይቆች  የታደለች  አገር  ነች፡፡
             ስለዚህ  በሃይቆችና  በወንዞች  አካባቢ  የተጠኑና  በአግባቡ

             የተቃዱ ከተሞችንና የመዝናኛ ሪዞርቶችን እንዲገነቡ በማድረግ
             ዜጎች ለኑሮ ምቹና ማራኪ በሆኑ አካባቢዎች እንዲኖሩ ጥረት
             ይደረጋል፡፡

             አብን በሚቀጥለው አስር  ዓመት ጣናሃይቅንየተንተራሰ ግዙፍ
             አማራጭ  የመዝናኛ፣  ኮንፈረንስ፣ዲፕሎማቲክ  እና  ቱሪዝም

             ከተማ  ለመገንባት  እቅድ  ይዟል፡፡  ጣና  ዙሪያ  ርዝመቱ  310
             ኪሎ ሜትር ሲሆን የጣና ዙሪያን በአግባቡ ለመጠበቅ የበፈር
             ዞን  በአንድ  ኪሎ  ሜትር  ራዲየስ  እንዲሰራ  ከተደረገ  በኋላ
             ከበፈር  ዞኑ  በኋላ  ዙሪያውን  አስፋልት  መንገድ  በመገንባት
             በርካታ ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዝ ከተማ ይገነባል፡፡ ጣና ኀይቅ
             ከሚገኝበት  ደጋማ  አካባቢ  አንጻር  የመዝናኛ  ሪዞርቶቹም
             ለቱሪስቶች  ምቹ  መሆን  ስለሚችሉ  በክልሉ  ካለው  የቱሪስት
             መስህቦች ጋር ተደምሮ ለአገሪቱም ከፍተኛ ገቢና ሥራ ዕድል

             መፍጠር  ይቻላል  ብሎ  አብን  ያምናል፡፡  በመሆኑም  አካባቢው
             አማራጭ  የኮንፈረንስ፣  ቱሪዝም  እና  የዲፕሎማቲክ                      ከተማ
             ይሆናል፡፡  በሌሎችም  የውኃ  አካላት  ተመሳሳይ  የልማት


             131    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   128   129   130   131   132   133   134   135   136   137   138