Page 129 - አብን
P. 129
አብን
አንድን ቦታ ለታቀደለት ዓላማ ለማዋል ሲፈለግ በቦታው ላይ
እየኖረ ያለው ሕብረተሰብ ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡
የነዋሪውን የኢኮኖሚና የማኀበራዊ መስተጋብር ያገናዘበ ጥናት
ላይ የተመሰረተ አማራጭ አስቀድሞ ማዘጋጀት የመንግስት
ግዴታ ነው፡፡ነገር ግን እስከ አሁን ባለው የመንግስት
እንቅስቃሴ አንድን ቦታ ለማልማት በሚል በቦታው ላይ ረጅም
ጊዜ የኖሩ ዜጎችን በጋራ ያፈሯቸውን የተለያዩ የኢኮኖሚና
የማኀበራዊ ተቋሞቻቸውን ያለ መተኪያ በማፍረስና
ነዋሪዎቹን ከቦታቸው በማፈናቀል በተለያዩ ለመኖሪያነት
ዝግጁ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ ተበታትነው እንዲሰፍሩ በማድረግ
የመተዳደሪያ ሥራና የገቢ ምንጭ እንዲቋረጥባቸው
ተደርጓል፣ እንደ እድርና እቁብ የመሳሰሉት ተቋሞቻቸው
እንዲጠፉ ተደርጓል፣ አዲስ በሚሰፍሩበት ቦታ እንደመንገድ፣
የትራንስፖርት አገልግሎት፣የውኃና የመብራት አቅርቦት
እንዲሁም የጤናና የትምህርት ተቋማት የመሳሰሉት
ባለመኖራቸው የተነሳ ከፍተኛ ለሆነ ኢኮሚያዊና ማኀበራዊ
ቀውስ የተዳረጉ ሲሆን ሁኔታው አሁንም ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች የልማት ተነሽዎችን
የሚያቅፍ እንጅ የሚያፈናቅል አይሆንም፡፡ ለዚህም ዘርፉ
የሚመራበት ዝርዝር አሰራር ይዘረጋል፡፡
ሠ.)ከተሞቻችን በጋራ ከሚገለፁባቸው ችግሮች ውስጥ ዋና
ዋና ከሚባሉት የማኀበረሰቡ አገልግሎቶች የጤናና የትምህርት
አገልግሎት ጥራት ችግሮች እንዲሁም በድህነትና በማኀበራዊ
ቀውስ ጎዳና ላይ የወጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችንና ጧሪ
የሌላቸው አረጋውያንን የሚታደጉ ተቋማት አለመኖራቸው
127 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !