Page 126 - አብን
P. 126

አብን


             ይሰራል፡፡በተጨማሪም             ለሕዝብ       ስትራቴጂካዊ         ጠቀሜታ

             ያላቸው የረቀቀ ቴክኖሎጂና ከፍተኛ ካፒታልን የሚጠይቁ ልዩ
             የኢንዱስትሪ ተቋማት እና ፓርኮች እንዲመሰረቱ ይደረጋል፡፡


                2.4.2  የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን
             ሀ) የከተሞች አስተዳደር እና አመራር
             በመጭዎቹ ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከገጠር ወደ
             ከተማ  መፍለሱ  የማይቀር  ጉዳይ  ነው፡፡  አብዛኛው  ሕዝባችን

             በግብርናው ዘርፍ በመሰማራቱ ምክንያት ግብርና ቀላል ግምት
             የማይሰጠው  ዘርፍ  ቢሆንም  የግብርናው  ድርሻ  እየቀነሰ
             በኢንዱስትሪና  በአገልግሎት  ዘርፉ  እየተተካ  መሄድ  ይገባዋል
             ብሎ  ንቅናቄያችን  ያምናል፡፡  ይህ  እንዲሆን  ደግሞ  ከተሞች
             ታቅደው  ሊገነቡ  ያስፈልጋል፡፡የከተማ  መሬት  አስተዳደር
             መዋቅራዊና  የፖሊሲ  ክለሳ  ያስፈልገዋል፡፡  አብን  መሬት

             የግል፣  የወልና  የመንግስት  በመባል  በሦስት  የይዞታ  ክፍፍል
             ውስጥ  መግባት  አለበት  ብሎ  ያምናል፡፡የሚደረገው  ማሻሻያ
             በአንድ  በኩል  እሴት  ሳይጨምሩ  መሬትን  በመያዝ  ብቻ
             የሚከብሩ አካላትን መስመር የሚያሲዝ መሆን ይገባዋል፡፡በሌላ
             በኩል  ግን  ግለሰቦች  መሬት  የመሸጥና  የመግዛት  መብታቸው
             መረጋገጡ  ለተፋጠነ  የከተማ  ዕድገት  ወሳኝ  መሆኑ  ታምኖ
             ይኼን  ዓይነት  ማሻሻያ  ያስፈልጋል፡፡  ይህም  የከተሞችን
             ዕድገት ከማፋጠኑም በተጨማሪም በከተሞች ዙሪያ ያሉ አርሶ

             አደሮችም  ከመሬቱ  ተጠቃሚ  መሆን  ያስችላቸዋል፡፡ከተሞች
             ራዕይ  ያላቸው፣  ህብረ-ብሔራዊነት  የተላበሱ፣በቴክኖክራት
             የሚመሩና ኢኮኖሚውን በአጠቃላይ የሚመሩ እንዲሆኑ ታቅዶ


             124    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   121   122   123   124   125   126   127   128   129   130   131