Page 123 - አብን
P. 123

አብን


                      ተቋማትን ማጠናከርና የሰው ኃብት ልማት


             2.3.3  የገጠር ልማት እና ሽግግር
             የገጠር ልማት እና ሽግግር ዋነኛ ዓላማ የአርሶ አደሩን የኑሮ
             ሁኔታ ማሻሻል ነው፡፡ይህም የአርሶ አደሩን ገቢ ከማሳደግ በላይ
             አርሶ አደሩ በአኗኗሩ እንዲቀየር ወይም እንዲሻሻል ይጠይቃል፡
             ፡አብን      አካታች       የገጠር      ልማት        (inclusive    rular
             development)  ፕሮግራሞችን  ተግባራዊ  በማድረግ  የአርሶ
             አደሩን  ኢኮኖሚያዊ፣  ማኅበራዊ  እና  ፖለቲካዊ  ተጠቃሚነት

             ያሳድጋል፡፡አብን  የአርሶ  አደሩ  ሕይወት  እንዲሻሻል  የገጠር
             ሽግግር      ስትራቴጅዎችን           ነድፎ      ተግባራዊ        ያደርጋል፡፡
             ስትራቴጅዎቹ  ከድህነት  ቅነሳ  በዘለለ  ቀጣይነት  ያለው  እና
             የገጠሩን  ማኅበረሰብ  ኁለንተናዊ  ብልፅግና  የሚያረጋግጡ
             አቅጣጫዎች          ናቸው፡፡አብን         ተግባራዊ        የሚያደርጋቸው
             ስትራቴጅዎች በዋናነት ትኩረታቸው፦

                  የገጠር ኢንተርፕራይዞችን ማበረታታት እ ናማሳደግ፤
                  የፋይናንስ  አቅርቦትን  ማሻሻል  (የገጠር  ባንኮች፣
                    መካከለኛና  አነስተኛ  የፋይናንስ  ተቋማት፣የግብርና
                    መድን ሰጭ ተቋማትወ.ዘ.ተ)
                  የእርሻ መካናይዜሽን
                  የገጠር  ከተሞችን  (ማዕከላት)  መገንባት፦  አርሶ  አደሩ
                    መተዳደሪያው  ግብርና  ቢሆንም  የኑሮው  ሁኔታ
                    መዘመን  አለበት፡፡አብን  ለአርሶ  አደሩ  መሰረተ  ልማት

                    ለመዘርጋት  በሚያመች  መልኩ  የአርሶ  አደሩን
                    አሰፋፈር  ወደ  አንድ  አካባቢ  በማሰባሰብ  ትናንሽ




             121    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   118   119   120   121   122   123   124   125   126   127   128