Page 119 - አብን
P. 119
አብን
ሞት የሚቀንስ ስትራቴጅ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡በተመሳሳይ
ሁኔታ የአገራዊ የእንስሳት ምርት ፍላጎትን ለማርካት የበለጠ
የንግዱን ስርዓት ዘመናዊ ማድረግና የማስተዋወቅ ሥራ
ይሰራል፡፡ በተለይ ሕጋዊ ነጋዴውን በማዳከም እና የአገርን ገቢ
እያሳጣ ያለው የድንበር ላይ ሕገ-ወጥ የእንስሳት ወደ ሌላ
አገር ማጓጓዝ የሚያስቀር የቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፡፡
የእንስሳት ጤና አገልግሎቱ በመንግስት ብቸኛ ተደራሽ
ስለማይሆን የግሉ ዘርፍ በስትራቴጂው ውስጥ በማካተት እና
በማበረታታት ተደራሽነቱን እንዲሰፋ ይደረጋል፡፡ ድንበር ዘለል
ተላላፊ በሽታዎች ፈጣን የክትትል እና ሰርቪላንስ ሥራ
በማካሄድ ምላሽ መስጠት፤ የእንስሳት መመገበያ ንጽህና
መጠበቅ፣ንጹህ ውሀ ማቅረብ እና ክትባት ማቅረብ ዋነኛ
የበሽታ ቅድመ መከላከል ስትራቴጅ ይሆናሉ፡፡
ወተት ምርት
የወተት ምርትን ለማሳደግ የተሸሻሉ ዝርያዎችን የማቅረብ እና
የማዳቀል ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
የማዳቀል አግልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ
በሆኑባቸው አካባቢዎች የአውራ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በዚህ
ዘርፍ የመንግስት ውስን አቅምን ለመሙላት ብቃት ያለቸውን
የግል ባለሀብቶች የብቃት ማረጋጋጫ በመስጠት ወደ ሥራው
የሚገቡበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
ዶሮ እርባታ
ዶሮ እርባታ ላይ በዋናነት ትኩረታችን የአገር ውስጥ ፍላጎትን
ማሟላት ሲሆን ምርቱ በመጠንም በጥራትም እየጨመረ
117 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !