Page 116 - አብን
P. 116

አብን


             2.3.1  የሰብል ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ


             የተሻሻሉ  የግብርና  አሰራሮችን  በመጠቀም  አሁን  ያለውን
             የሰብል  ምርትና  ምርታማነት  ማሳደግ  ያስፈልጋል፡፡  የግብርና
             ኤክስቴንሽን  አገልግሎት  አሰጣጥን  አሁን  ያለንበትን  ደረጃ
             በማገናዘብ  ማዘመን፣አርሶ  አደሩ  ትክክለኛ  የሆነውን  የግብዓት
             መጠን እና አይነት እንዲጠቀም የምክር አገልግሎት መስጠት፣
             ለሥነ-ምኅዳሩ ተስማሚ የሆነ የሰብል ምርጥ ዘር እና ሌሎች
             ግብዓቶችን  በጥራት፣በመጠን  በወቅቱ  ማቅረብ፣  ለአርሶ  አደሩ

             ለግብዓት እና ቴክኖሎጅ ብድር ማቅረብ፣ የአፈር አሲዳማነትን
             ማከም  ለምርታማነት  እድገቱ  ቁልፍ  ተግባር  በመሆናቸው
             ትኩረት  ተሰጥቶ  ይሰራባቸዋል፡፡  ለግብርና  ምርምር  ሥራው
             ትኩረት  በመስጠት  ምርምሩ  ሥነ-ምኅዳርን  መሠረት  ያደረገ
             ምርታማ፣                          በሽታን                       እና
             ድርቅንየሚቋቋምየሰብልዝርያእናዘመናዊየግብርናአሰራሮችንበም

             ርምርማውጣት፤የሌሎችን በማላመድ ላይ ትኩረት                         አድርገው
             እንዲሰሩ  ይደረጋል፡፡በተለይ  በአሁኑ  ወቅት  ለሰብል  ልማቱ
             ዘርፍ ማነቆ የሆነውን የሰብል ምርጥ ዘር እጥረት ለመፍታት
             ለግል  ሴክተሩ  ድጋፍ  በማድረግ  በድርጅቶች፣በባለሀብትና
             በሞዴል  አርሶ  አደሮች  የሚባዛበትን  ሁኔታ  ማመቻቸት
             ይገባል፡፡  ለሰብል  በሽታ፣አረም  እና  ተባይ  ቁጥጥር  ሊረዱ
             የሚችሉ  በአካባቢ  ላይ  የሚያደርሱት  ተጽኖ  ዝቅተኛ  የሆነ
             ኬሚካሎች  በወቅቱ  ማቅረብ፣ዘመናዊ  የምርት  መሰብሰቢያና

             ድኅረ ምርት ቴክኖሎጅ በማቅረብ በድህረ ምርት እና በቡቃያ
             ደረጃ  በሚደርስ  ጉዳት  እና  ብክነት  የሚመጣውን  ምርት
             መቀነስ ስለሚያስቀር ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራበታል፡፡


             114    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   111   112   113   114   115   116   117   118   119   120   121