Page 113 - አብን
P. 113
አብን
እና የፋይናንስ ተቋማትን መደበኛ የውስጥ አሰራሮችን
የተመለከተ ክትትል እና ቁጥጥር የሚያካሄድ በመሆኑ
የፋይናንስ ዘርፉ በተገቢው መንገድ እንዳያድግ እንቅፋት
ሆኗል፡፡ በመሆኑም አብን፦
ብሔራዊ ባንክ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ ተቋም
(independent institution) ይሆን ዘንድ አሁን ካለው
ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ እና የሚንስትሮች ምክር ቤት
ተጠሪነት ወጥቶ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለተወካዮች ምክር
ቤት ሆኖ እንዲቋቋም ያደርጋል፡፡
ብሄራዊ ባንክ በዋናነት የብርን የመግዛት አቅም
የተረጋጋ እንዲሆን፣ የዋጋ ግሽበትን የመከላከል እና
የመቆጣጠር፣ የሥራ አጥ ቁጥር ዝቅተኛ እንዲሆን
እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር
የሚያስችል የሞኒተሪ ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም ባንኮች፣ የፋይናንስ ገበያዎችን፣ ማይክሮ
ፋይናንስ ተቋማትን ሌሎች የገንዘብ ተቋማትን
መመቆጣጠር እና ማስተዳደር በሚችልበት አደረጃጀት
እንዲዋቀር ይደረጋል፡፡
የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ቁጥጥር በተመለከተ ራሱን
የቻለ ባለስልጣን መስሪያ ቤት እንዲቋቋም በማድረግ
ዘርፉ በተሻለ አቅም እንዲንቀሳቀስ ይደረጋል፡፡
ሊበራላይዜሽን በተመለከተ
ዘርፉ ለውጭ የፋይናንስ ተቋማት ዝግ በመሆኑ እና የውጭ
አገር ዜጎች በዘርፉ እንዳይሳተፉ ገዳቢ ሕግ በመኖሩ የውጭ
ካፒታል ፍሰት እንዳይኖር እና ለትላለቅ ኢንቨስትመንት
111 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !