Page 110 - አብን
P. 110
አብን
በ2009/2010 ዓ.ም ባንኮች ያበደሩት የገንዘብ መጠን (ቦንድን
ጨምሮ) 618.6 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን 25 በመቶ
ዓመታዊ እድገት አሳይቷል፡፡ አብዛኛው ብድርም ለማዕድን፣
ኃይልማ መንጫና ውኃ ልማት (በአብዛኛው በቦንድ)፣
ኢንዱስትሪ፣ ሆቴልና ቱሪዝም እና ለዓለም አቀፍ ንግድ ዘርፍ
የተሰጠ ነው፡፡ በዓመቱ የቁጠባ መጠን ደግሞ 639.5 ቢሊየን
የደረሰ ሲሆን 29.6 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡
የባንክ ቅርንጫፎች በዓመቱ ከ3647 ወደ 4461 እድገት
አስመዝግበዋል፡፡በዚህም የባንክ ቅርንጫፍ ለሕዝብ ያለው
ምጣኔ 1 ቅርንጫፍ ለ27555 ከነበረበት ቀንሶ 1 ቅርንጫፍ
ለ21651 ሰዎች ሆኗል፡፡
አብን የፋይናንስ ሥርዓቱ ብቁ እና ዓለምአቀፍ ተወዳደሪ
ይሆን ዘንድ መዋቅራዊ (structural) እና ዘርፋዊ (sectoral)
ለውጥ (reform) እንዲተገበር ያደርጋል፡፡ለውጡ በዋናነት
የሚከተሉት አላማዎችን ለማሳካት ይተገበራል፡፡
የሞኒተሪ ፖሊሲ ዓላማዎችን ለማሳካት፤
የፋይናንስ አገልግሎቱን ለማስፋት እና ለማሰራጨት፤
ለኢኮኖሚያዊ እድገት እና ልማት ምቹ ሁኔታን
ለመፍጠር፤
ፍትኃዊ የሆነ የውድድር ሥርዓትን ለማበረታታት፤
የፋይናንስ ገበያ ለማልማት እና ለማሰደግ፤
ሥርዓታዊ ውድቀት (systemic failure) እንዳይመጣ
ለመከላከል እና ለመቆጣጠር፤
ለነፃ ገበያ ሥርዓት ሽግግር ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
108 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !