Page 114 - አብን
P. 114

አብን


             የብድር  አቅርቦት  እጥረት  ዳርጓል፡፡በመሆኑም  ድርጅታችን

             ዘርፉን  ለማሳደግ  ይረዳ  ዘንድ  የሀገር  ውስጥ  የፋይናንሰ
             ተቋማትን በመደገፍ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ
             ዘርፉ  ለውጭ  ተቋማት  እና  የውጭ  አገር  ዜጎች  ክፍት
             እንዲሆን የሚያስችል የፖሊሲ እርምጃዎችን ይፈፅማል፡፡

                  የፋይናንስ         ሥርዓቱን         አካታችነት         (Financial
                    inclusion) በተመለከተ
             የፋይናንስ ሥርዓቱ አካታች ይሆን ዘንድ የፋይናንስ ተቋማት

             በቴክኖሎጅ  ታግዘው  ለሁሉም  የማኅበረሰብ  ክፍሎች  ተደራሽ
             እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡የፋይናንስ ተቋማት ተደራሽ ብቻ ሳይሆን
             አነስተኛ  ገቢ  ላላቸው  የማኅበረሰብ  ክፍሎች፣  ለወጣት  ሥራ
             ፈጣሪዎች  እና  ለአርሶ  አደሩ  የብድር  አቅርቦት  እንዲያገኙ
             የሚያስችሉ የፖሊሲ ማዕቀፎችን ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡


                  የማያሰሩ ሕግና አሰራሮችን ማስወገድ (Deregulation)
                    በተመለከተ
             ለውጭ  ካፒታል  ፍሰት  ማነቆ  የሆኑ  እና  መደበኛ  ፋይናንስ
             ተቋማት  ሥራዎችን  የተመለከቱ  አሰሪ  ያልሆኑ  ሕጎች  እና
             አሰራሮችን  በማስወገድ  (Deregulation)  ለፋይናንስ  ሥርዓቱ
             ምቹ  የሥራ  ሁኔታ  እንዲፈጠር  የሚያስችል  የሕግ  ማዕቀፍ
             እንዲኖር ያደርጋል፡፡


             ለ. የጣልቃ ገብነት ፓሊሲ
             በማደግ  ላይ  ባሉ  ሃገሮች  በኢኮኖሚው  ወስጥ  ጣልቃ  ገብነት
             ወሳኝ  ከመሆኑ  አንፃር          በገበያ  ውስጥ  ጉድለት  በሚታባቸው
             አቅርቦቶች  እንዲሁም  በረዥም  ጊዜ  ገቢ  ሊገኝባቸውና  በግሉ

             112    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   109   110   111   112   113   114   115   116   117   118   119