Page 109 - አብን
P. 109
አብን
የአገሪቱን የተዛባ የፋይናንስ ሥርዓት ለመገንዘብ ይረዳ ዘንድ
የተወሰኑ መረጃዎችን መመልከት ተገቢ ነው። በ2012 ዓ.ም
ጥቅል ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ወደ 20 በመቶ ያደገ ሲሆን
የምግብ ዋጋ ንረትም ወደ 18 በመቶ ደርሷል፡፡ ለዋጋ ግሽበቱ
የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መደረጉ አስተዋጽኦ
አድርጓል፡፡ የብር ከዶላር አንጻር እንዲዳከም የተደረገው
የውጭ ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በሚል ምክንያት
ቢሆንም በውጭ ዘርፍ ያሳየው ውጤት ግልጽ አይደለም፡፡
መንግስት የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲያደረግ የዋጋ
ግሽበት እንዳይጨምር በፋይናንስ ዘርፉ ጠበቅ ያለ ፓሊሲ
ለመተግበር ጥረት አድርጓል፡፡ ከነዚህም መካከል የንግድ
ባንኮችን በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡትን መጠን ከነበረበት
5 በመቶ ወደ 7 በመቶ የማሳደግ ሥራ የተሰራ ሲሆን
አማካይ የቁጠባ ወለድ መጠንም ከ5.4 በመቶ ወደ 8 በመቶ
እንዲሁም የብድር ወለድ ከ12.8 በመቶ ወደ 14.3 በመቶ
እንዲያድግ እንዲሁም የብድር ጣራ የመወሰን ሥራም
ተሰርቷል፡፡ ይህን በማድረግ የገንዘብና የብድር አቅርቦት
እድገት የተገደበ እንዲሆን አደርጓል፡፡ የገንዘብ አቅርቦትን
ቁጥጥር ጠበቅ የማድረግ እርምጃ ከመከናወኑ በፊት
በ2009/10 ዓ.ም የገንዘብ አቅርቦት ዓመታዊ እድገቱ ወደ 30
በመቶ አካባቢ ሆኖ 602 ቢሊየን ብር፣ የብድር እድገትም 30
በመቶ አካባቢ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ወቅት
ዓመታዊ ጥቅል ምርት እድገቱ 18 በመቶ አካባቢ ነበር፡፡
107 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !