Page 107 - አብን
P. 107
አብን
የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ አስራር ለማሻሻልና የኢኮኖሚ ምህዳሩን
ለውድድር ምቹ እንዲሆን ለማድረግ በአስተዳደራዊም ሆነ
በፖለቲካዊ ድጋፍ የሚቋቋሙ የፖርቲ የሞኖፓሊ ተቋሞች
እንዳይኖሩ አበክረን እንሰራለን፡፡ በዚህ መልክ የተቋቋሙትንም
በመንግሥት ቁጥጥር ስር በማድረግ ወደ ግሉ ዘርፍ በግልፅ
የጨረታ ስርዓት እንዲዛወሩ እናደርጋለን፡፡ የተዋሃደ ሀገራዊ
ገበያ እንዳይኖር ገቺ የሆኑ የኢኮኖሚ እና የንግድ አሠራር
ልምዶች እንዲሻሩ እናደርጋለን፡፡ በዚህም ሂደት በገበያው
ውስጥ አግባብ ያለው ውድድር (Fair Competition)
እንዲኖር፣ የግል ዘርፉ ያላቋረጠ እድገት እንዲኖረው፣ የገበያ
ተዋንያዎች እንዲነቃቁ እና እንዲጠናከሩ ለማድረግ
ያለማለሳለስ እንሰራለን፡፡
የምናደርገው የኢኮኖሚ ተሃድሶ (Reform) ዋነኛ አንጓ
የንብረት ባለቤትነት መብት የሚከበርበት ስርዓት እውን መሆን
እና የሃገሪቱ የሃብት ድልድል (Resource Allocation) የገበያ
መር መሆኑን በማረጋገጥ ላይ የሚመሰረት ነው፡፡ ይህ ዓይነት
የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር በገበያ ውስጥ የምርት
መገልገያዎች በነፃ የሚዘዋወሩበት፣ በገበያ ተዋንያዎች
መካከል የሚካሄደው ውድድር በህግና እና በስርዓት
የሚመራበት፣ በገበያ ውስጥ የመቆየትና ያለመቆየት ጉዳይ
የሚወስነው በገበያ ውድድር ብቻ እንጅ የፖለቲካ አድልኦ
የማይኖርበትን ሁኔታ እውን በማድረግ ላይ ነው፡፡
በአጠቃላይ አብን የመንግሥት ሥልጣን ሲይዝ ልዩልዩ
የፖለቲካና የማህበረሰብ አደረጃጀትን ባሳተፈ መንገድ እንደ
105 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !