Page 108 - አብን
P. 108

አብን


             ማህበረ-ፖለቲካው  ሁሉ  በኢኮኖሚው  ውስጥም  ተቀራራቢ

             ሀገራዊ  ራዕይና  መስመር  እንዲኖር  ያደርጋል፡፡  ስለዚህ
             የኢኮኖሚ  ሥርዓታችን  ሀገራዊ  ዕቅድ  /national  planning/
             ኖሮት  በዚያ  ማዕቀፍ  ውስጥ  ግን  የግለሰቦችና  የድርጅቶች
             ኢኮኖሚያዊ  ነፃነት  እጅጉን  ለድርድር  በማይቀርብ  መንገድ
             መፈጸም  ይገባዋል፡፡  ከዚህ  ጋር  በተገናኘ  የአዕምሯዊ  መብት
             ጥበቃዎችን በማጠናከርና በማዘመን ፈጠራ የኢኮኖሚው ዋነኛ
             ሞተር  እንዲሆን  ይደረጋል፡፡በሚቀጥሉት  አምስት  ዓመታት
             ኢንዱስትሪው  ቀላል  የማይባል  ድርሻ  እንዲይዝና  የተደራጀ

             የከተሞች አገልግሎት ሰጭዎች እንዲስፋፉ ይደረጋል፡፡

                  3.  የፋይናንስ ሥርዓት/ የፋይናንስ ዘርፍ
             በአንድ አገር ውስጥ ቀጣይነት ያለው እና በፅኑ መሰረት ላይ
             የቆመ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ልማት ለማምጣት ጠንካራ
             እና  የተረጋጋ  የፋይናንስ  ሥርዓት  መዘርጋት  ግድ  ይላል፡፡

             አገራችን  ኢትዮጵያ  በአሁን  ጊዜ  እጅግ  ደካማ  የፋይናንስ
             ሥርዓት  ካላቸው  አገራት  መካከል  በግንባር  ቀደምትነት
             የምትጠቀስ ናት፡፡ የተቆጣጣሪ አካሉ ማለትም የብሔራዊ ባንክ
             አቅም       ውሱንነት፤         የፋይናንስ       አገልግሎቱ         በዋናነት
             የተንጠለጠለው  በጥሬ  ገንዘብ  ሥርዓት  ላይ  መሆን፤
             አገልግሎት  ሰጭ  ተቋማት  ብቁ  እና  ተወዳዳሪ  አለመሆን፤
             የፋይናንስ  ሥርዓቱ  አወቃቀር  የኢንቨስትመንት  ባንኮች፣

             የካፒታል  እና  ጠንካራ  የገንዘብ  ገበያ  የሌሉበት  መሆን
             (money market)፤ የፋይናንስ ሥርዓቱ አካታች እና ተደራሽ
             አለመሆን፤ የቁጥጥር ሥርዓቱ ገዳቢ (restrictive) እና የውጭ
             ካፒታል  ፍሰትን  የሚገታ  መሆኑ  በመሠረታዊነት  የሚጠቀሱ
             ችግሮች ናቸው፡፡

             106    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   103   104   105   106   107   108   109   110   111   112   113