Page 112 - አብን
P. 112
አብን
ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት እና የሥራ እድል
ለመፍጠር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ብሎም ለዚሁ
የሚረዳ የተቀላጠፈ የፋይናንስ አቅርቦት የሚያቀርቡ
የኢንቨስትመንት ባንኮች እንዲቋቋሙ የሚያስችሉ
የፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
የገንዘብ ምንዛሬ ገበያ፦አሁን ባለው የአገሪቱ ሞኒተሪ
ፖለሲ የገንዘብ ምንዛሬ የሚወሰነው በብሔራዊ ባንክ
በመሆኑ እና አቅርቦቱም አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ
የሆነ ገንዘብ ኢ-መደበኛ በሆነው በተለምዶ ጥቁር ገበያ
(black market) በሚባለው የገንዘብ ምንዛሬ ገበያ
ይዘዋወራል፡፡ድርጅታችን የብር ዋጋ አላግባብ
እንዳይወርድ እና ከፍ እንዳይል እንዲሁም የተረጋጋ
የምንዛሬ ምጣኔ ይኖር ዘንድ ተገቢ የሆኑ ሞኒተሪ
ፖሊሲ እርምጃዎችን በየጊዜው የሚወስድ መሆኑን እና
የምንዛሬው ምጣኔ በነፃ ገበያ ይወሰን ዘንድ የገንዘብ
ምንዛሬ ገበያ በሂደት ለነፃ ገበያ ክፍት እንዲሆን
ያደርጋል፡፡
የቁጥጥር እና አስተዳደር ሥርዓት (Regulation and
supervision) በተመለከተ
አሁን ላይ በአገሪቱ ያሉትን የፋይናንስ ተቋማት የማስተዳደር
እና የመቆጣጠር አጠቃላይ ኃላፊነት ያለበት ብሔራዊ ባንክ
ነው፡፡ ብሄራዊ ባንክ በስሩ ባሉ የሥራ ክፍሎች አማከኝነት
የፋይናንስ ተቋማትን በየዘርፋቸው ቁጥጥር እና ክትትል
ያደርጋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ የአቅም ውስንነት እንደተጠበቀ
ሆኖ በዋና ዋና የሞኒተሪ ፖሊሲዎች ከማተኮር ይልቅ ዝርዝር
110 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !