Page 117 - አብን
P. 117
አብን
በአሁኑ ወቅት እየተጀመሩ ያሉ የግብርና ማቀነባበሪያ
ኢንዱስትሪዎች ታሳቢ ያደረገ ጥሬ እቃ በመጠንና በጥራት
ማቅረብ ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ ኢንዱስትሪዎችን ሊመግቡ
የሚችሉ የምርት አቅም ያላቸውን አካባቢዎች በመለየት አርሶ
አደሮች ከፋብሪካዎች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግ
ጥራት ያለው ምርት በማቅረብ በዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑና
ፋብሪካዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነት
ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
አገራችን በከፍተኛ መጠን እና ደረጃ በመስኖ ውኃ ሊለማ
የሚችል መሬት እንዲሁም ለዚሁ ተግባር የሚሆን የውኃ
አቅም ስላላት ትላልቅ መስኖዎች በመገንባት የመስኖ ግብርና
እንዲስፋፋ ይደረጋል፡፡ይህም ከመኸር ምርት በተጨማሪ አርሶ
አደሩ በበጋ ሁለት ጊዜ እንዲያመርት ያስችላል፡፡ ለመስኖ
ልማቱ በዓለምአቀፍ ገበያ ሊቀርቡ የሚችሉ የአትክልት እና
ፍራፍሬ ዝርያዎችን በማቅረብ ጥራት ያለው እና ተወዳዳሪ
ምርት በማምረት እና በማቀነባበር ለገበያ እንዲቀርብ
የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፡፡ በዘርፉ የግል ባለሀብቱ
እንዲሰማራ አሁን ያለውን ረጅም ቢሮክራሲ በማስወገድ
ባላሀብቱ በቀላሉ ብድር፣ መሬት እና የባንክ ሌተር ኦፈ
ክሬዲት እንዲያገኝ ስርዓት ይዘረጋል፡፡
በቆላማው አካባቢ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን ያሉበትን ሁኔታ
በማጥናት መሬቱን ወስደው ወደ ምርት የገቡትን ባለሀብቶች
ድጋፍ ማድረግ፤ መሬቱን ወስደው ወደ ሥራ ያልገቡም ሆነ
115 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !