Page 120 - አብን
P. 120
አብን
ሲመጣ የውጭ ገበያን ታሳቢ አድርጎ እንዲሰራ ይደረጋል።
እንደ ሀገር የውጭ ምንዛሬ ለማዳን እና በዘርፉም ሰፊ የሆነ
የስራ እድል ለመፍጠር የምክር፣የጤና አገልግሎቶች
ውጤታማነት እና ጥራት እንዲሁም የመኖ አቅርቦት፣ የጤና
(ክትባት) እናየተሻሻሉ ዝርያ ማቅረብ የሚያስችል ሥርዓት
ይዘረጋል። የግሉ ሴክተር ግብዓት፣ የጤና አገልግሎት
በማቅረብ እና ምርት በማቀነባባር ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርግ
ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡
ቆዳና ሌጦ
ኢትዮጵያ ሰፊ የእንስሳት ኃብት ያላት አገር እንደመሆኗ
ከፍተኛ ቆዳና ሌጦ ወደ ውጭ የመላክ አቅም ቢኖራትም
አሁን ያለው ከፍተኛ የሆነ የጥራት ችግር ተግዳሮት ሆኖ
ቆይቷል፡፡ ይህንንም በመፍታት ለዓለምአቀፍ ገበያዎች የበለጠ
ተደራሽ ማድረግ ይቻላል። የምክር አገልግሎት፣ ማበረታቻ፣
ብድር ማመቻቸት፣ የጥራት ደረጃዎችንና መመሪያዎችን
በማመቻቸት ጥራት ያለው ምርት ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል
ሥርዓት ይዘረጋል። በምርቶች ላይ እሴት መጨመርና ለገበያ
ማቅረብ ተጨማሪ የሥራ እድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ
በአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በሚቀርብበት ወቅት ከጥሬ
እቃው የበለጠ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ እሴት
ለሚጨምሩ አካላት የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፡፡
የቁም እንስሳት እና ስጋ
በአሁኑ ወቅት የቁም እንስሳት ወደ ውጭ ከሚላከው
የእንስሳት እና እንስሳት ተዋጽኦ ምርት ክፍል ከፍተኛውን
118 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !