Page 135 - አብን
P. 135
አብን
የቱሪዝም መዳረሻዎችና የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት
ልማትን በተመለከተ
ሀ. የቱሪዝም መዳረሻ ልማት የፖሊሲ አቅጣጫዎች
ነባር መዳረሻዎችን በተመለከተ፡-
የቱሪዝም ልማቱን በተገቢው ሀኔታ ለማስኬድ ነባር
የቱሪስት መዳረሻዎችን ለቱሪስቱ እርካታን በሚፈጥር
መልኩ በሰው ኃይል፣ በቁሳቁስና በመሰረተ ልማት
ብቁ እንዲሆኑ ይሰራል፡፡ ይህም ሲባል የቱሪዝም
ልማቱ ስኬታማነት የቱሪስት መስህቡ ባለበት ቦታ
ብቻ ሳይሆን መስህቦቹን በሚያስተዳድረው የመንግስት
ቢሮና በተዋረድ ባሉ መስሪያ ቤቶች ብቁና የዘርፉ
ባለሙያዎች ሳይሆኑ ከተቀመጡ የፖለቲከኛ ሹመኞች
በማጽዳት በባለሙያዎች የሚመራ ሆኖ እንዲደራጅ
ይሰራል፡፡ ይህ አደረጃጅትም የመስህብ ስፍራዎችን
በሚያስተዳድረው የጥብቅ ስፍራና ቅርስ አስተዳዳሪ
(Destination Management Organizations and
Destination managers) አካል ጭምር የሚተገበር
ሆኖ የቱሪዝም ልማት ሥራውን በሚያሳልጥ መልኩ
እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡
የነባር መዳረሻዎችን በሰው ኃይልና ቁሳቁስ
የማስተሳሰር ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጅ የተደገፈ
የመረጃ ቋት እንዲኖር መመሪያ ይዘጋጃለታል፡፡ ይህም
133 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !