Page 142 - አብን
P. 142
አብን
የአካባቢ እንክብካቤና ጥበቃ ኢንተርፕራይዞች
(environmental conservation and
protection Enterprises) እንዲቋቋሙና
በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲደግፉና
አካባቢውንም እንዲጠብቁና እንዲንከባከቡ
ለማድረግ የሚያስችል የማበረታቻ ሥራዎች
ይሰራሉ፡፡ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍም ይደረጋል፡፡
ይህም የአካባቢውን ማኅበረሰብና ወጣት ባማከለ
መልኩ እንዲተገበር ይደረጋል፡፡
በመዳረሻዎች አካባቢ የሚለሙ የቱሪዝምና
ሆቴል እንዲሁም ሌሎች የኢንቨስትመንት
ሥራዎች የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትና የማጣራት
ደረጃ ዓለምአቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ
እንዲዘጋጅና ተፈፃሚ እንዲሆን ይሰራል፡፡ የሕግ
ማዕቀፍም ይዘጋጅለታል፡፡
የጥብቅ ስፍራዎች እንክብካቤና የቅርሶች
እድሳት የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚሰራ
ሥራ ይሆናል፡፡
ሠ. የዱር እንስሳትና ኢኮ-ቱሪዝም
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ኃብት ከታደሉት አገራት በግንባር
ቀደምትነት የሚትጠቀስ ናት፡፡ ከባሕላዊና ታሪካዊ ቅርሶች
በተጨማሪ የተለያዩ ጥብቅ ክልሎች፣ ብሔራዊ ፓርኮች፣
የተፈጥሮ ደኖች፣ ኃይቆችና ወንዞች ባለቤትም ናት፡፡
140 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !