Page 91 - አብን
P. 91
አብን
የተረጋጋ የገበያ ዋጋ እንዲኖር ማስቻል (የአብዛኛዎቹ
ሃገሮች አመታዊ የዋጋ ግሽበት ከ 2 በመቶ በታች
እንዲሆን ነው፡፡)
የተሟላ የስራ እድል ለዜጎች እንዲፈጠር ማስቻል
(የስራ አጥነት ቁጥር ከ 4 በመቶኛ እንዳይበልጥ
ማስቻል)፡፡
የተረጋጋና ቀጠይነት ያለው የምጣኔ ሃብታዊ እድገት
ማምጣት ማስቻል (2-3 በመቶኛ አመታዊ አጠቃላይ
ሃገራዊ የምርት ውጤት (GDP) እድገት )፤
ሃገሪቱ ከሌሎች የአለም አቀፍ ሃገራት በሚኖራት
ግብይት የተስተካከለ ሚዛናዊ ክፍያ (Balance of
Payment) እነዲኖራት ማድረግ ፤
ከነዚህ በተጨማሪም፡-
ከባቢያዊ ብክለትን መቆጣጠር፤
በምርት ሂደት የሚፈጠሩ አሉታዊ ውጫዊ ተፅኖዎችን
(negative externalities) መቀነስ፤
ድህነትን (Poverty) እና ኢ-እኩልነትን (inequality)
በመቀነስ የተሻለ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን (equity)
ማምጣት፤
ምርታማነትን ማሳደግ (labour productivity)፤
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሕዝብ ፋይናንስ ላይ ጥብቅ
ቁጥጥር ማድረግና በአግባቡ ማስተዳድር ማስቻል
የማክሮ ኢኮኖሚክ ፓሊሲ ዋና አላማ እየሆነ
መጥቷል፡፡
89 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !