Page 90 - አብን
P. 90

አብን


             ኢንዱስትሪው  ቀላል  የማይባል  ድርሻ  እንዲይዝና  የተደራጀ

             የከተሞች አገልግሎት ሰጭዎች እንዲስፋፉ ይደረጋል፡፡

             2.2     ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ
             መንግስት  በመሰረታዊነት  የሚከተላቸው  ማክሮ  ኢኮኖሚክ
             ፓሊሲዎችን  በሁለት  ክፍሎች  ከፍለን  ማየት  ይቻላል፡፡
             ይኸውም  ፍላጎትን  መሰረት  ያደረገ  ፓሊሲ  እና  አቅርቦትን
             መሰረት  ያደረገ  ፖሊሲ  ናቸው፡፡  በፍላጎት  በኩል  ያሉ  ማክሮ
             ኢኮኖሚክ  ፓሊሲ  በዋናነት  የገንዘብ/ሞኒተሪ  ፓሊሲ                        እና

             የበጀት/ፊሲካል         ፓሊሲ       ተበለው        በሁለት       ይከፈላሉ፡፡
             የበጀት/ፊሲካል ፓሊሲ ግብርን፣ የመንግስት በጀት አጠቃቀምን
             እና ብድርን       መሰረት በማደርግ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን
             አጠቃላይ ፍላጎት መለወጥና መቆጣጠር መቻልን ይፈልጋል፡፡
             የገንዘብ/ሞኒተሪ ፓሊሲ            ደግሞ በዋናነት         ገንዘብ አቅርቦትና
             ፍላጎትን እነዲሁም የወለድ ምጣኔን መቆጣጠርና ማስተዳደር

             ተቀዳሚ  ትኩረቱ  ናቸው፡፡በሌላ  በኩል  አቅርቦትን  የማከሉ
             ፖሊሲዎች  ገበያ  ተኮር  እና  ጣልቃ  ገብነት  ብለን  በሁለት
             እናያቸዋለን፡፡ ገበያ ተኮር ፓሊሲዎች አብዛኛወን ግዜ አሰራር
             ማሻሻያዎች  ማድረግን፣  በቀደም  የነበሩ  አንዳንድ  የሃገሪቱ
             ፓሊሲዎችን መለወጥን፣ ግብር ቅነሳ መድረግ ጋር ይያያዛሉ፡፡
             ጣልቃገብነት  ፓሊሲ  ከትምህርት፣  ጤና  ፤መሰረተ  ልማት
             እንዲሁም የግብርና፣ ኢንዱስትሪ ፓሊሲና ቲክኖሎጅ ሴከተር
             ፓሊሲዎች ማሻሻያ ማድረግ ጋር ይያዛል፡፡ የነዚህ ሁሉ ማክሮ

             ኢኮኖሚ ፓሊሲዎች  አብዛኛውን ጊዜ አላማቸውም፡-






               88   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   85   86   87   88   89   90   91   92   93   94   95