Page 89 - አብን
P. 89

አብን


                  የግሉ  ዘርፍ  ተጠናክሮ  እስከሚወጣበት  ጊዜ  መንግስት

                    ምርምርን  በማጠናከር  እና  በማስፋፋት  ረገድ  ሚናው
                    ወሳኝ  ስለሆነ  በዚህ  ረገድ  የመንግስት  ኢንቨስትመንት
                    የሚበረታታ ይሆናል፡፡
                  በመንግስት  ስር  ባሉ  ተቋሞች  አማካኝነት  የገንዘብና
                    የፊስካል  ፖሊሲዎችን  በማውጣት፣  በመተግበር  እና
                    አፈፃፀምን በመከታተል ረገድ ተገቢ ሚናውን እንዲወጣ
                    ይደረጋል፡፡
                  መንግስት  ይፋዊ  እና  ይፋዊ  ያልሆኑ  ይሁንና  የግል

                    ገበያው  የሚሰራበትን  ማህበራዊ  ምህዳር  የሚገዙትን
                    ደንቦች  ህግጋትና  ተቋማዊ  አሰራሮችን  ተግባራዊ
                    የሚያደርጉበትን  ሁኔታ  በመፈተሽ  እና  በመቆጣጠር
                    ማሻሻል  እና  መታረም  የሚገባቸውን  በማረም  ተገቢ
                    ማናውን እንዲወጣ ይደረጋል፡፡


             በአጠቃላይ  አብን  የመንግሥት  ሥልጣን  ሲይዝ  ልዩልዩ
             የፖለቲካና  የማህበረሰብ  አደረጃጀቶችን  ባሳተፈ  መንገድ  እንደ
             ማህበረ-ፖለቲካው  ሁሉ  በኢኮኖሚው  ውስጥም  ተቀራራቢ
             ሀገራዊ  ራዕይና  መስመር  እንዲኖር  ያደርጋል፡፡  ስለዚህ
             የኢኮኖሚ  ሥርዓታችን  ሀገራዊ  ዕቅድ  /national  planning/
             ኖሮት  በዚያ  ማዕቀፍ  ውስጥ  ግን  የግለሰቦችና  የድርጅቶች
             ኢኮኖሚያዊ  ነፃነት  እጅጉን  ለድርድር  በማይቀርብ  መንገድ
             እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ የአዕምሯዊ መብት

             ጥበቃዎችን በማጠናከርና በማዘመን ፈጠራ የኢኮኖሚው ዋነኛ
             ሞተር  እንዲሆን  ይደረጋል፡፡  በሚቀጥሉት  አምስት  ዓመታት




               87   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   84   85   86   87   88   89   90   91   92   93   94