Page 82 - አብን
P. 82
አብን
ምዕራፍ 2
የኢኮኖሚውን ዘርፍ በተመለከተ የአብን መፍትሄዎች
2.1. ጠቅላላ
የአብንየኢኮኖሚ ራዕይ በመካከለኛ ገቢ የእድገት ደረጃ የደረሰች
የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ሆኖ ማየት ነው፡፡የኢትዮጵያ
የወደፊት የኢኮኖሚ እድገት እና አጠቃላይ የልማት ስኬት
ቀጣይነት ባለው፣ የተነቃቃ፣ የማናቸውንም መሰናክል
መቋቋም የሚችል፣ ሊኖር በማይችል የነፃ ገበያ መርሆ
ሳይሆን ግልፅነት ባለውከፖለቲካ ጣልቃገብነት የፀዳ፣
በውድድር ላይ በተመሰረተ የገበያ ኢኮኖሚ መርሆዎች
የሚመራ የኢኮኖሚ እድገት እውን ሆኖ ማየት ነው፡፡
የዚህ ኢኮኖሚ ስርዓት ውጤትም ጥቂቶችን ብቻ የሚያበለፅግ
ሳይሆን ትሩፋቱን ለብዙሃኑ የሚያጋራ ሆኖ፣ ኃላፊነቱ እና
ተደራሽነቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለብዙኃኑ የሚጠቅም
የዳበረ ህብረተሰብን መፍጠር የሚያስችል ሆኖ ማየት ነው፡፡
ስለሆነም ኢኮኖሚውን በተመለከተ አብን ዓይነተኛ መፈክር
በውድድር ላይ ተመሰረተ የተሟላ የገበያ ኢኮኖሚ በመካከለኛ
ገቢ ደረጃ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ሁና ማየት የሚል
ነው፡፡
አብን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያሳድግ እና
የሚያሳትፍ፣ በማህበራዊ ፍትህ አመለካከት የተቃኜ የኢኮኖሚ
ልማት ትልም በመከተል ብቻ ነው የሃገሪቱን ዘርፈ ብዙ
የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለማቃለል
80 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !