Page 73 - አብን
P. 73

አብን


             የሚሻ ነው፡፡ በመብት አፈጻጸም ረገድ እንኳ የሀይማኖት ጉዳይ

             ስስና ኮርኳሪ መሆኑን መዘንጋት አይገባም፡፡

             ትህነግ  መራሹ  የኢህአዴግ  መንግስት  ከምስረታ  ጀምሮ
             አንግቦት  በነበረው  ሶሻሊስት  ዘመም  የአቢዮታዊ  ዴሞክራሲ
             ርዕዮት  ምክንያት  ማህበረሰብንና  እምነትን  ለይቶ  በመፈረጅ
             ጥሰቶችን  ሲፈጽም  መቆየቱ  ይታወቃል፡፡  በዚህ  ረገድ

             ኢትዮጵያን  እንደሀገር  በተለይም  የኢትዮጵያን  ትላንት፤
             ከሀይማኖቶች  መካከል  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ክርስትናን
             ከመነሻው  ጀምሮ  ፈርጆ  በጠላትነት  ምድብ  አስቀምጦ  በርካታ
             ጉዳቶችን  አድርሷል፡፡  ከዚህ  ጋር  በተያያዘ  መታወቅ  ያለበት
             መሰረታዊ  ጭብጥ  ትህነግ  መራሹ  መንግስት  የክርስትና
             እምነትን  ሲፈርጅ  ከልብ  የእስልምና  ሀይማኖትን  ወይም  ሌላ
             እምነትን ወገን አድርጎ አይደለም፡፡ የመንግስቱ ባህርያት ከላይ
             የተገለጹት  እንደመሆናቸው  መጠን  የሙስሊሙን  ማህበረሰብ

             መብቶች  መጋፋትና  መጣስ  ለፖለቲካ  ፍጆታው  አዋጭ
             በሆኑለት  ጊዜ  የመብት  ገፈፋውንና  ጥቃቱን  አጠናክሮ  በይፋ
             ሲፈጽም ነበር፡፡

             በህገመንግስቱ  ውስጥ  በአንቀጽ  11  ስር  የተደነገገው
             የመንግስትና የሀይማኖት መለያየት ጉዳይ እንዲሁም በአንቀጽ
             27  ስር  የተደነገጉት  የሀይማኖት  ነጻነቶችን  የሚመለከቱ

             ጉዳዮች  አለም  አቀፍ  መርሆዎችን  በተከተለ  አግባብ
             ተፈጻሚነት  እንዲኖራቸው  የህግ  አውጭው  አካል  ዝርዝር
             ህግጋትን ማውጣት እንዳለበት እንገነዛባለን፡፡ ሆኖም እስካሁን
             የሀይማኖት  ጉዳዮችን  ለማስተዳደር  በሚል  የወጣ  ምንም
             አይነት  ህግ  የለም፡፡  በዚህ  ምክንያት  በሀገራችን  ውስጥ


               71   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   68   69   70   71   72   73   74   75   76   77   78