Page 68 - አብን
P. 68

አብን


             አብን  አሁን  የተንሰራፋው  የጥላቻ  ትርክት  ተወግዶ  ምህዳሩ

             ብዝሀነትን       ባከበረ      ሀቀኛ     ስርአት፣       በወንድማማችነት፣
             በእኩልነት፣  በፍትህና  በዴሞክራሲ  የተቃኘ  የፖለቲካ  ምህዳር
             እንዲፈጠር ጥረት ያደርጋል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ ላለፈው
             ስህተትና  ችግር  እውቅና  እንዲሰጥ፤  ለዚህም  የሽግግር  ፍትህ
             ስርአት  እንዲዘረጋ  በማድረግ  ለቀጣዩ  ሂደት  መደላድልን
             መፍጠር  ነው፡፡  ይሄን  ተከትሎ  ለአሁኑና  ለወደፊቱ  ሊያሰራ
             የሚችል  አዲስ  ማህበራዊ  ውል  መግባት  ያስፈልጋል፡፡  ይህ
             አዲስ  የሆነ  የሁሉም  ባለድርሻ  አካላት  ተሳትፎና  ይሁንታ

             የተረጋገጠበት ሕገመንግስት እውን ማድረግን ይመለከታል፡፡

             የድርድርና  የሰፊ  ማህበራዊ  ስምምነት  ውጤት  ሆኖ
             የሚመጣው  ሕገመንግስት  ሀገራችንን  አንቆ  ከያዛት  የተበላሸ
             የፖለቲካ  ባህል  ወደፊት  ሊያራምዱ  ይችላሉ  ተብለው
             የሚጠበቁ  መሰረታዊ  መርሆዎችን  የያዘና  በተለይ  ስምምነት

             ላይ     የማይደረሰባቸውን           በርካታ      ማህበራዊና        ፖለቲካዊ
             እንዲሁም         ኢኮኖሚያዊ         ጉዳዮች        እያስታረቁ        ወይም
             እንደሁኔታው  ገለልተኛና  ተጨባጭ  በሆነ  መልኩ  እየዳኙ
             መቀጠል  የሚቻልባቸውን  ስነ-ስርአታዊ  ድንጋጌዎች  የያዘ
             ይሆናል፡፡  በአጭሩ  ቀጣዩ  የኢትዮጵያ  ሕገመንግስት  መርህ
             ተኮር  /prescriptive/  እና  ስነስርዓታዊ  /procedural/  ይዘቶች
             ይኖሩታል፡፡  በሕገመንግስቱ  ጥቅል  ይዘቶች  ዙሪያ  ስምምነት

             ከተደረሰ፣  ሕገመንግስቱን  በማርቀቅና  በማጽደቅ  ሂደት
             ሳይንሳዊና  ነባራዊ  ሁኔታዎችን  ከግምት  ውስጥ  ያስገቡ
             አሰራሮችን  መሰረት  በማድረግ  ሁሉንም  አካላት  ሊያግባባና
             ወደፊት  ሊያራምድ  የሚችል  ስርአት  መገንባት  እንደሚቻል
             ቅድመ  ግምት  መውሰድ  ይገባል፡፡  በተጨማሪ  ሕገመንግስት

               66   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   63   64   65   66   67   68   69   70   71   72   73