Page 67 - አብን
P. 67

አብን





                                        ክፍል ሁለት
                                    የአብን መፍትሄዎች
                                       ምዕራፍ-1.

                                    በፖለቲካ መስክ


             1.1.   ጠቅላላ

             የአማራ       ህዝብ      የፖለቲካ       ንቅናቄ      አንድምታ        ውስጥ
             መሰረታዊው አጀንዳ አማራ ተኮር ህግና ሥርዓት ሰራሽ የሆኑ

             ጭቆናዎች  መፈጸማቸውን  እና  የቀጠሉ  መሆኑን  በመገንዘብ
             ሁሉም  በእኩል  የሚስተናገድበት  ስርዓት  ለመገንባት  ሀቀኛ
             ትግል  ማድረግ  ነው፡፡  ከሁለተኛው  የጣሊያን  ወረራ  ወቅት
             የሚነሳ  ሆኖ  በጥራዝ  ነጠቆች  “የጨቋኝ  ተጨቋኝ”  ስሁት
             ትርክት  ሲሰራጭ  ቆይቶ  በሂደት  የህገ  መንግስትና  የመዋቅር
             ሽፋን  ተሰጥቶት  የተተገበረውን  አውዳሚ  የፖለቲካ  ምዕራፍ
             መዝጋት አስፋላጊ እንደሆነ አብን በጽኑ ያምናል፡፡


             የምናደርገው  ትግል  በህዝባችንና  በሀገራችን  ላይ  የተደቀኑትን
             ዘርፈብዙ       ችግሮች       በዘላቂነት       ለመፍታት         የሚያስችሉ
             መሰረታዊ  ለውጦችን  ማምጣት  አማራጭ  የሌለው  ጉዳይ
             እንደሆነ  እንረዳለን፡፡  ስለሆነም  በቅርቃር  ውስጥ  ያለው
             የሀገራችን  የማህበረ-ፖለቲካ  ሁኔታ  የሚስተካከለው  ሁሉን
             አካታች  የሆነ  ብሄራዊ  የውይይትና  የድርድር  መድረክ
             በመክፈት  ሁላችንንም  አሸናፊ  የሚያደርግ  ፍትሀዊ  አማካይ

             ላይ መድረስ ሲቻል ብቻ ነው፡፡


               65   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   62   63   64   65   66   67   68   69   70   71   72