Page 65 - አብን
P. 65

አብን


              በተላላፊ በሽታና ከአመጋገብ ጉድለት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

              በወሊድና  በህፃንነት  ደረጃ  የሚሞቱ  ህፃናት  ብዛት  የሃገሪቱን
              የጤና  አገልግሎት  ዝቅተኛነት  ያመለከታሉ፡፡  የሃራችን
              የህክምና መስጫ ተቋማትና የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት
              በዝቅተኛ  ደረጃ  ላይ  የሚገኝ  ነው፡፡  የሃገራችን  የጤና  ዘርፍ
              በሚመደብለት በጀት አናሳነት የሚቀርበው የጤና አገልግሎት
              የተዳከመ  ነው፡፡  የጤና  አገልግሎት  መስጫ  ተቋማት
              አነስተኛነት  ሚዛን  የጠበቀ  ሃገራዊ  ስርዓት  አለመኖር፣
              የሚሰጡት  አገልግሎቶች  ስብጥር  አነስተኛነት  በዘርፉ  ያሉ

              ጉልህ  ችግሮች  ናቸው፡፡  የንፁህ  መጠጥ  ውሃ  አቅርቦትና
              የመፀዳጃ  አገልግሎት  ዝቅተኛነት  ለሃገራችን  የጤና  ችግሮች
              መግዘፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ናቸው፡፡

             3.3.   የመሠረተ ልማት አለመስፋፋት


              በኢትዮጵያ  የመሠረት  ልማት  ዝርጋታ  በዝቅተኛ  ደረጃ  ላይ
              የሚገኝ  ከመሆኑም  በላይ  በክልሎች  መካከል  ያለው
              ስርጭትም  ሚዛናዊ  እና  ፍትሃዊ  አይደለም፡፡  በኢትዮጵያ
              የመንገድ  ስራን፣  የመብራት  ሃይልን፣  የንፁህ  መጠጥ  ውሃ
              አቅርቦት፣  የመገናኛ  አገልግሎት  በማስፋፋት  ረገድ  ጥረት
              ቢደረግም፣  በእነዚህ  መስኮች  እስካሁን  ወጪ  የተደረገው
              መጠን ከፍተኛ ቢሆንም፣ የኢኮኖሚው እድገት የሚጠይቀውን

              የሚያሟላ አይደለም፡፡ በመሰረተ ልማት ረገድ ያለው ክፍተት
              ከፍተኛ  መሆኑ፣  ለተከታይ  ዓመታት  በዘርፉ  ከፍተኛ
              ኢንቨስትመንትን  የሚጠይቅ  ነው፡፡  የመሠረት  ልማቱን
              ለማስፋፋት  የተሰጠው  ትኩረት  የተገነባው  መሠረተ  ልማት




               63   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   60   61   62   63   64   65   66   67   68   69   70