Page 64 - አብን
P. 64

አብን


             3.   ዘላቂ     ለውጥ        ሊያስመዘግብ         ያልቻለ       የማህበራዊ
                  አገልግሎት ዘርፍ
             3.1.   ትምህርት

              አሁን በሥራ ላይ ያለው የትምህርት ፖሊሲ እንደሃገሪቱ ህገ
              መንግስት ሁሉ፣ የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ እምነት ማስፋፊያ
              ነው፡፡  የሃገራችን  የትምህርት  ዘርፍ  ዋነኛው  ችግር

              የትምህርት  አመራር  ከባለሙያዎች  እጅ  ወጥቶ  በካድሬዎች
              አመራር  ስር  እንዲወድቅ  በመደረጉ፣  በተገቢ  ሙያ  የሰለጠነ
              ሃገር  ተረካቢ  ትውልድ  ለማፍራት  ያልቻለ  ዘርፍ  ነው፡፡
              በስርዓተ  ትምህርት  ቀራፂውም  ሆነ  መምህራን  ምልመላ፣
              ቅጥር፣ ሥልጠና እድገትና ዝውውር ለገዥ ፓርቲ ፓለቲካዊ
              እምነት ማጎብደድ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው መዘዘኛ ከሆነ
              ቆይቷል፡፡


              የሃገሪቱ የትምህርት ምዘና ፓሊሲ፣ የሰለጠኑ በቂ መምህራን
              አለመኖር፣ የተማሪ እና የትምህርት ጥምርታ፣ የተማሪ እና
              የክፍል ጥምረት ያልተመጣጠነ መሆን፣ በዩኒቨርሲቲዎች እና
              በሁለተኛ  ደረጃ  ት/ቤቶች  የሚሰጠው  ትምህርት  ጥራት
              በእጅጉ  የወረደ  መሆን፣  ዩኒቨርሲቲዎቹ                  የምርመር  ሥራ
              የማይካሄድባቸው  መሆን  በአጠቃላይ  የትምህርት  ስርዓቱ
              በተማሪ  ብዛት  ላይ  እንጅ  ጥራት  ላይ  እንዳያተኩር  መደረጉ

              በዘርፉ የሚታዩ ጎላ ጎላ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡

             3.2.   ጤና

              ሃገራችን  ኢትዮጵያ  በሽታ  የተንሰራፋበት  ሀገር  ናት፡፡

              በሃገራችን  ካሉት  የጤና  ችግሮች  ከ80%  በላይ  የሚሆኑት

               62   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   59   60   61   62   63   64   65   66   67   68   69