Page 63 - አብን
P. 63
አብን
ዓይነት መብቶችን መነፈግ ነው፡፡ አሁን ሃገራችን ባለችበት
ሁኔታ ዲሞክራሲን በማዋለድ መልካም አስተዳደር ማስፈን
ካልተቻለ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተዘፈቀበት ድህነት
የሚወጣበት መንገድ የተዘጋ ነው፡፡
2.14. የቱሪዝምን ዘርፍ መዳከም
ሃገራችን የረዥም ዘመን ታሪክ ባለቤት፣ ልዩ ልዩ የተፈጥሮ
ሃብቶች ያሏት፣ የበርካታ ማህበረሰቦች ሃገር እንደመሆኗ
በርካታ ባህሎች አሏት፡፡ ይህ ግዙፍ አለኝታ ነው፡፡ ይሁንና
ለዚህ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ደካማ በመሆኑ አገልግሎቱ
የሚጠይቀውን የተመቻቸ መሰረተ ልማት በበቂ ሁኔታ
ባለማቅረባችን፣ ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ግንባታ ሊያበረክት ይችል
ከነበረው እጅግ በጣም ዝቅተኛውን መጠን ነው እስካሁን
በጥቅም ላይ የዋለው፡፡ የሚጎበኙ ስፍራዎች በበቂ ሁኔታ
ጥራትና መጠን ያለማመቻቸት ትልቁ ችግር ሲሆን፣ በተላይ
ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ከአዲሱ የኮቪድ ወረርሽኝ
በተጨማሪ ገዥው ፓርቲ ህግን ባለማስከበር ብቻ ሳይሆን
የሚከተለው ጽንፈኛ የዘውግ ፓለቲካ የሃሪቱን ፀጥታ እና
ሰላም ጥያቄ ውስጥ የከተተ በመሆኑ የዘርፉ እድገት
ተግዳሮት ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ነው፡፡
61 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !