Page 58 - አብን
P. 58
አብን
መንግስት ሥልጣን ከመያዙ ከሶስት ዓመት በፊት
ማለትም ከ2006 እስከ 2009 በነበረው ጊዜ የብር ዋጋ
እንዲቀንስ የተደረገበት መጠን በ33.94 በመቶ ነበር፡፡
አሁን በሥልጣን ሊይ ያለው የብልፅግና መንግስት
በስልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሶስት ዓመታት
ማለትም ከመጋቢት 2010 እስከ የካቲት 2013 ባሉት
ዓመታት የብር ዋጋ የቀነሰበት መጠን በ47.17 በመቶ
ነው፡፡ በህወሓት መራሹ መንግሥት የመጨረሻ
የስልጣን ዘመን ማብቂያ ወር ላይ ማለትም መጋቢት
2010 የ1 የአሜሪካ ዶላር የባንክ የመሸጫ ዋጋ
27.76 ብር ሲሆን፣ በአሁን ወቅት ማለትም በየካቲት
2013 የ1 የአሜሪካ ዶላር የባንክ የመሽጫ ዋጋ
40.89 ብር ነው፡፡ በአንፃሩ በየካቲት 2013 ወር የ1
ዶላር የጥቁር ገበያ ዋጋ እስከ 57 ብር ደርሷል፡፡ ይህ
የምንዛሬ ሁኔታ በገበያ ተወሰነ ይባል እንጅ፣
መንግሥት ሆነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋሞች
በሚያሳየው የተንበርካኪነት አቋም ምክንያት
የተከናወነ ነው፡፡
ለገፅታ ግንባታ ሲባል በአዲስ አበባ የሚካሄዱ ትልልቅ
ፕሮጀክቶች (የወንዝዳር ልማት 28 ቢሉዮን ብር፣
የለገሃር ፕሮጀክት 30 ቢሉዮን ብር) የተመደበው 58
ቢሊዮን ብር ነው፡፡ መንግሥት ይህን ገንዘብ ከበጀት
ሳይሆን ከብሄራዊ ባንክ እየተበደረ ከሆነ፣ ይህ ብድር
በተጨማሪ ገንዘብ ህትመት የሚታገዝ ስለሆነ፣ በዋጋ
ንረት መጨመር ሊይ ቀጥተኛና ከፍተኛ ተፅእኖ
ይኖረዋል፡፡
56 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !