Page 53 - አብን
P. 53
አብን
ሚዛን መዛባት የሃገሪቱን የውጭ ብድር ጫና በከፍተኛ ደረጃ
እየጨመረው በመሄድ ላይ በመሆኑ፣ የካቲት ወር 2013
በወጡ መረጃዎች መሰረት በ2012 የሸቀጦች የወጪ ንግድ
የገቢ ንግድ የወጪ የመሸፈን አቅሙ ወደ 15% አካባቢ
መድረሱ የሃገሪቱ የንግድ ሚዛን ከፍተኛ የአደጋ ምልክት
እየታየበት መሆኑ ይስተዋላል፡፡
የሀገሮችንና የግዙፍ ኩባንያዎችን የእዳ ጫና እንዲሁም እዳ
የመመለስ አቅምን በመገምገም የምዘና ደረጃ በማውጣት
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁት ድርጅቶች መካከል ሙዲስ
የተባለው ተቋም በግንቦት ወር 2012 በወጣው የምዘና
ሪፖርት የኢትዮጵያን እዳ የመክፈል አቅም ዝቅ አድርጎ
በመመዘን ሀገራችንን ከፍተኛ የወጭ እዳ ካለባቸው ሀገሮች
ምድብ ከቷታል፡፡ ፊች (Fitch) የተባለው ተቋም በካቲት
2/2013 ባወጣዊ ሪፖርት ደግሞ ኢትዮጵያ የውጭ እዳ
የመክፈል ግዴታቸውን ሊያቋርጡ ከሚችሉ ከፍተኛ ስጋት
ከደቀኑ ሀገሮች ተርታ የሚያስመድባት (CCC) ደረጃ
ስጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ከግል የውጭ
አበዳሪዎች እዳ የመክፈያ ጊዜ እፎይታና ማራዘሚያ
ለመጠየቅ ማቀዱን አመልክቷል፡፡
ለዘላቄታው የሃራችን የገቢ እና ወጪ ንግድ ሚዛንም ሆነ
የመጠባበቂያ ክምችት ከውጭ ብድርና እርዳታ ጥገኝነት
መላቀቅ እስከልቻለ ድረስ፣ ኢኮኖሚው ለከፍተኛ ችግር
መጋለጡ እና ይህም ችግር ወደ ፖለቲካ ቀውስ ማምራቱ
የማይቀር ነው፡፡
2.8. የኮሰመነ የመዋዕለ ነዋይ (ኢንቪስትመንት) መጠን
51 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !