Page 57 - አብን
P. 57

አብን


             ባለፉት  ሶስት  ዓመታት  የዋጋ  ንረት  በከፍተኛ  ደረጃ

             መጨመርና  ኑሮ  ውድነት  መባባስ  መንግስት  የህውሓት
             ደጋፊዎች  እና  የአሻጥረኛ  ነጋዴዎች  ስግብግብ  ባህሪ
             በምክንያትነት         ሲያቀርብ        ቆይቷል፡፡        ይሁንና       እነዚህ
             ምክንያቶችለዋጋ  ንረቱ  መባባስ  ከአንድ  እና  ሁለት  በመቶ
             በላይድርሻ ያላቸው አይደለም፡፡ እውነተኛውና ወደ 98 በመቶ
             የሚሆነውን  ምክንያት  ያበረከቱት  መንግሥት  የሚከተላቸው
             ከህዝብ የኑሮ ሁኔታ ጋር ያልተዛመዱ ፖሊሲዎች ናቸው፡፡


             እርግጥ  በኮሮና  ወረርሽኝ  ምክንያት  በዓለም  አቀፍ  ደረጃ
             የተዛባው  የአቅርቦት  ሰንሰለት  (Supply  Chain)  መቀዘቀዝ፣
             በአነስተኛ  ደረጃ  የዋጋ  ንረቱ  መባባስ  በምክንያትነት  ሊጠቀስ
             ይችላል፡፡  ይሁንና  ዋነኛዎቹ  ለዋጋ  ንረቱ  መባባስ  አስተዋፅኦ
             እያደረጉ ያሉት የመንግሥት ፖሊሲዎች የሚከተለት ናቸው፡፡
                    ዋናው  እና  ቀደም  ካለ  ጊዜ  ጀምሮ  ከፍብሎ  የነበረው

                     ይበልጡኑ  ያባባሰው  ከየካቲት  ወር  2013  ጀምሮ
                     በተከታታይ ለሁለት ጊዜ በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ
                     ጭማሪ ነው፡፡
                    መንግሥት  ያጋጠመው  የውጭ  ምንዛሬ  እጥረት
                     አንዱ  ዋነና  ምክንያት  ነው፡፡  በእጥረቱ  ምክንያት
                     መንግሥት  በነዳጅ  ላይ  ያደርግ  የነበረውን  ድጎማ
                     በ25%  መቀነሱ  ለዋጋ  ንረቱ  መባባስ  ከፍተኛ
                     አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

                    የብር      ዋጋ     ከሌሎች        ሀገራት      ገንዘቦች       ጋር
                     የሚመነዘርበት  ዋጋ  እንዲቀንስ  መደረጉ  የዋጋ  ንረቱ
                     መባባስ  አይነተኛ  ተጠያቂ  ነው፡፡  የአብይ  አህመድ


               55   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   52   53   54   55   56   57   58   59   60   61   62