Page 55 - አብን
P. 55

አብን


              በመቶ ነው፡፡ ይህም የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ሀገሪቷ

              የተመቻቸ ሁኔታ እንደሌላት የሚያመለክት ነው፡፡

             2.9.   ከፕራይቬታይዜሽን ጋር የተያያዙ ችግሮች
             ሀገራችን  ኢትዮጵያ  በ1960ዎቹ  መጨረሻ  ላይ  ወደ
             ኅብረተሰባዊ ሥርዓት ስትገባ በግል ተይዘው የነበሩ የቢዝነስና
             አገልግሎት  ሰጭ  ተቋማት  ወደ  መንግስት  እንዲዛወሩ

             ተደርጓል፡፡ከእነዚህም  ውስጥ  ብዙዎቹን  ኢህአዴግ  ያለዋጋ
             ውድድር  ቸብችቧቸዋል፡፡  እነዚህ  ተቋማት  ከሥራ  ዕድል
             ፈጠራ፣ከሀገራዊ  ምርት  አስተዋጽዖና  በሌሎችም  ኢኮኖሚያዊ
             መለኪያዎች ሲገመገሙ በመንግስት ሲመሩበት ከነበረው በባሰ
             ሁኔታ ተዳክመዋል፡፡

             በህዝብ  ግፊት  ከዚያው  ቡድን  ውስጥ  በመውጣት  የለውጥ
             ኃይል  ነኝ  የሚለውም  ቡድን  ቢሆን  ኃላፊነት  የጎደላቸው

             ኢኮኖሚያዊ  ውሳኔዎችን  እያሳለፈ  ይገኛል፡፡ከላይ  የተጠቀሰው
             ጠባብ  ቡድን  ካፒታል  እስከሚያከማች  ድረስ  ወደ  ግል  ዘርፍ
             ሳያዘዋውር        ያቆያቸውን         የልማት፣የምርትና           አገልግሎት
             ተቋማትን ደርሶ በድንገት ለመሸጥ እየተንደረደረ ይገኛል፡፡

             2.10.  በዋጋ  ንረት  ማሻቀብ  የህዝቡ  ኑሮ  መጎዳት  እና
                    የድህነት መባባስ


              የዋጋ  ንረት  እያሻቀበ  መሄድ  ቋሚ  ደሞዝተኛውን  እና
              በዝቅተኛ  የኑሮ  ደረጃ  ላይ  የሚገኘውን  የህብረተሰብ  ክፍል
              የሚጎዳ  ነው፡፡  በአብን  እምነት  ባለፉት  ሰላሣ  አመታት
              ኢኮኖሚው  በከፋተኛ  መጠን  አደገ  በተባለባቸው  ዓመታትም


               53   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   50   51   52   53   54   55   56   57   58   59   60