Page 54 - አብን
P. 54
አብን
ቀድሞውንም ቢሆን የሀገራችን ኢንቨስትመንት በበቂ የቁጠባ
መጠን ያልተደገፈ እንዳልነበር ይታወቃል፡፡ የሃገር ውስጥ
ቁጠባ ከጠቅላላው ብሔራዊ ምርት ያለው ድርሻ በየጊዜው
እያሽቆለቆለ መምጣቱ በግልፅ ይታያል፡፡ የሃገሪቱ የነፍስ
ወከፍ ገቢ በኑሮ ውድነት እየተጠቃ በማሽቆልቆል ላይ
በመሆኑ የዜጎች የመቆጠብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ
በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በተላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት የሃገሪቱ ሰላም እና ፀጥታ
የተናጋበት የፖለቲካ መረጋጋት ሊታይ ያልቻለበት ሁኔታ
ስለነበር የግልም ሆነ የመንግሥት ኢንቨስትመንት ሊበረታታ
የሚችልበትን ሁኔታ አልፈጠረም፡፡ የአንድ ሃገር የእድገት
መነሻ የካፒታል ምሥረታ ነው፡፡ በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ
የካፒታል ምስረታ ምንጭ የሃገር ውስጥ ቁጠባ መሆን
ሲገባው የቁጠባው መጠን በኢኮኖሚው መቀዛቀዝ ምክንያት
እየቀነሰ ሄዷል፡፡ የቁጠባው መቀነስ የግሉንም ሆነ
የመንግሥት ኢንቨስትመንት መጠን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ
እያስደረ ነው፡፡ ይኸ ሁኔታ ደግሞ የሃገሪቱ የመዋዕለነዋይ
በውጭ ብድርና እርዳታ ላይ ጥገኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የሃገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ የውጭ
ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ የፖለቲካ መረጋጋት የሌለበት
ሁኔታ ከመሆኑም በላይ፣ የግል ቢዝነስ ለማቋቋም ሀገሪቱ
ያላት አመችነት ከሰሃራ በታች ካሉት ሀገራት ጋር እንኳን
ሲነፃፀር ዝቅ ያለ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከሰሐራ በታች ያሉት
ሀገሮች አማካይ ደረጃ 51.61 ሲሆን፣ የኢትዮጵያ 49.06
52 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !